ሳፋሪኮም 'ኤምፔሳ ግሎባል' በተሰኘው በዓለም አቀፍ የክፍያ ስርዓቱ ኢትዮጵያን ማካተቱ ተገለጸ። የኬንያው የስልክ ኔትዎርክ ኦፕሬተር የሆነው ሳፋሪኮም በ 'ኤም-ፔሳ ግሎባል' በተሰኘው አገልግሎቱ ኢትዮጵያን ማካተቱ ተገልጿል። ይህም ደንበኞች ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ ልውውጥ እንዲያደርጉ የሚያስችላቸው ነው ተብሏል። በኬንያ ያሉ ደንበኞች አሁን በኤም-ፔሳ ኢንተርናሽናል ሪሚታንስ በኩል ወደ M-Pesa ኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ ማስተላለፍ ይችላሉ ተብሏል። በዚህ ትብብር፣ ሁለቱም ሀገራት ያሉ ደንበኞች የ M-Pesa ዋሌት ብቻ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ይህም በኬንያ የሚኖሩ እና የሚሰሩ ኢትዮጵያውያንን እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚኖሩና የሚሰሩ ኬንያውያን ይጠቅማል ተብሏል። የM-Pesa ኬንያ ደንበኞች ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ190 በላይ አገሮች በኤም-ፔሳ ግሎባል አገልግሎት አማካኝነት ገንዘብ መላክ እና መቀበል ይችላሉ ተብሏል።[ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8] @Ethiocrypto_433 @Ethiocrypto_433
October 16, 2024 33