CJMATH: post #213 — TG.ME

በኢትዮጵያ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ታሪክ እጅግ አነጋጋሪ የሆነ ዝቅተኛ ውጤት ተመዘገበ:: በአገር አቀፍ ደረጃ ይፋ የተደረገውን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ተከትሎ፣ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ሰፊ አጀንዳ የሆነና በርካታ ተከታታዮችን ያስገረመ የውጤት ዝርዝር ይፋ ሆኗል። በማኅበራዊ ሚዲያ የመረጃ ገጾች (ጉርሻ ፔጅን ጨምሮ) ከተሰራጩት የውጤት ሰነዶች ማረጋገጥ እንደተቻለው፣ በሶሻል ሳይንስ (Social Science) ዘርፍ ፈተናውን የወሰደው የ22 ዓመት ወንድ ተፈታኝ፣ ከጠቅላላ 600 ነጥብ 20.67 ብቻ በማስመዝገብ በአማካይ 3.45% አስመዝግቧል። ይህም በኢትዮጵያ የትምህርት ታሪክ ውስጥ በታችኛ ደረጃ ከተመዘገቡት ውጤቶች መካከል እጅግ አነስተኛው እና ያልተለመደው ተብሎ ተጠቅሷል።

August 26, 2026 79 1