ሹመት ═✦═ ✍ ሙሉጌታ ተስፋዬ (አያ ሙሌ) ' ሹመቴ ... ሺ ሞቴ ... እሱም እንደ ልቡ ... እኔም እንደ… — ከስነ-ፅሁፍ ዓለም — TG.ME

ሹመት
═✦═
ሙሉጌታ ተስፋዬ (አያ ሙሌ)
'

ሹመቴ ... ሺ ሞቴ ...
እሱም እንደ ልቡ ... እኔም እንደ አሞቴ
ባይልም ዳሞቴ
እንደ ክራሞቴ

ቢፈቅደኝ ... ሊያሞኘኝ ...
ቢያቅደኝ ... ቢመኘኝ ...

እኔ ምን ተዳዬ ... ሁሉም ያሻው ቢሆን ...
ስንቄንና ትጥቄን ሳይሰጠኝ ... ላይሸኘኝ ...
አሜን ብዬ ካደርኩ ... ምን አለ እሚሳነኝ

አሀዱ ለፍቅር ... ለሰላም ሽልማት
ምን አለ ልዕልና ... ከጣር ከህማማት

ዕድሜ እየነገረ ... ልብ እየሰገረ ...
እጅ እየጋገረ ... ቀን እየማገረ ...

ቢሾሙም ... ጥንስስ ነው
ቢመጡም ... እንጥስ ነው
ቢሄዱም ... ብጥስ ነው
ቢኖሩም ... ቅንጥስ ነው

እሁ ..... ተነፈስኩ
ፈሰስኩ .....
እንደ ደም ባልረጋም ...
ካልተሾምኩ አልሰጋም።

═════════
📔 የባለ ቅኔ ምህላ
🗓 2003 ዓ.ም.
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/Ethiobooks
Telegram
ከስነ-ፅሁፍ ዓለም
✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል! የቻናላችን https://t.me/Ethiobooks ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ። ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ @firaolbm እና @tekletsadikK ተጠቀሙ።
👍4🙏2😁1🤔1
August 14, 2026 1.4K 2