ወ ታ ደ ር 👨‍🎨 👨‍🎨 👨‍🎨 ወታደር፣ ዋቶ አደር። 👨‍🎨 ወታደር ባለቃው፣ ባላገር በጭቃው።… — ከስነ-ፅሁፍ ዓለም — TG.ME

ወ ታ ደ ር
👨‍🎨 👨‍🎨

👨‍🎨
ወታደር፣ ዋቶ አደር።

👨‍🎨
ወታደር ባለቃው፣ ባላገር በጭቃው።

👨‍🎨
ለወታደር በቅሎ፣ ለተማሪ ቆሎ።

👨‍🎨
ወታደር አወራውረኝ፣ ገበሬ አቆጣጥረኝ።

👨‍🎨
ወታደር ሲደኸይ፣ ጃኖ ያዘወትራል።

👨‍🎨
ዘንጋዳና ወታደር፣ በመኸር ጊዜ ይታይ ነበር።

👨‍🎨
ወታደር ቢበደር፣ ባላገር ይካስ።

👨‍🎨
ጦርነትን ከወታደር፣ ወሬን ከባላገር።

👨‍🎨
ለወታደር ሰፊ መንደር፣ ለወንዲላ መልካም ዱላ።

👨‍🎨
ሞኝ ወታደር፣ ሚስቱን ጥሎ መንደር።

👨‍🎨
ወታደር ሲያረጅ፣ አቃቤ ይሆናል።

👨‍🎨
ባጠፋ ወታደር፣ ይክሳል ባላገር።

👨‍🎨
በቅሎ ማዋስ ለወታደር፣ ሸማ ማዋስ ለባላገር።

👨‍🎨
የወታደር ፈዛዛ፣ የእናት ነዝናዛ፣ የሴት ቀበዝባዛ።

👨‍🎨 👨‍🎨
ነገር በምሳሌ

@ethiobooks
👍8
August 12, 2026 1.4K 5