━ ስልታዊ ማፈግፈግ ━
(Strategic Retreat)
━━━━✦━━━━
✍ ዶ/ር ኢዮብ ማሞ
'
ስልታዊ ማፈግፈግ (Strategic Retreat) ማለት አንድን የጀመርነውን ነገር ርግፍ አድርጎ መተው ማለት አይደለም። ለወደፊት በብቃት ለመንቀሳቀስ ሲባል ለተወሰነ ጊዜ በብልሃት ወደ ኋላ ማፈግፈግ ማለት ነው።
በሕይወት ውስጥ አንዳንዴ ለማሸነፍ ምርጡ መንገድ ወደ ፊት መግፋቱን መቀጠል ሳይሆን፤ ቆም ብሎ ማሰብ፣ ሁኔታዎችን መገምገም፣ ከተጎዳንበት ነገር ማገገም እና እራስን እንደገና ማዘጋጀት ነው።
ስልታዊ ማፈግፈግ ማለት ጥንካሬን ለመጠበቅ፣ ግልጽነት ለማግኘት እና ለወደፊት ለተሻለ ውጤታማነት ለመዘጋጀት ሆን ተብሎ የሚወሰን ጊዜያዊ ዝምታ፣ ከነገሮች ዘወር የማለት፣ የመውጣት፣ የመቆም ወይም አቅጣጫን የመቀየር ውሳኔ ነው።
ይህ ማለት፦
✔️ ማቋረጥ ሳይሆን፣ መስተካከል (recalibrating) ነው።
✔️ ፍርሃት ሳይሆን፣ ጥበብ ነው።
✔️ መሸነፍ ሳይሆን፣ ለተሻለ የላቀ ግስጋሴ መዘጋጀት ነው።
"አንዳንዴ ትልቁን ስእል ለማየት ወደ ኋላ ማፈግፈግ ያስፈልጋል" እንደሚባለው ማለት ነው።
መቼ ነው ስልታዊ ማፈግፈግን ማሰብ ያለብን?
1. ወደ ፊት መቀጠል አላስፈላጊ ጉዳት ሲያስከትል፦
አንዳንድ ጊዜ ሁኔታው ውስጥ መቆየት የስሜትን ወይም የአካልን ጥንካሬ ሲያሟጥጥ መለስ ማለት ጥሩ ነው።
2. ግልጽነት እና አቅጣጫ ስንፈልግ፦
አንዳንድ ጊዜ ሕይወት ግራ ሲያጋባን፣ “ትክክለኛ አቅጣጫ ላይ ነኝ?" ብሎ ለመጠየቅ ማፈግፈግ አስፈላጊ ነው።
3. ዝለት (Burnout) ሲሰማን፦
አንዳንድ ጊዜ ብዙ ለፍተን ጥቂት ስናገኝ፣ ከመሯሯጣችን የተነሳ ውስጣችን ሲደክም መረጋጋት ያስፈልጋል።
4. መርዛማ (Toxic) ሰዎች ሲበዙብን፦
አንዳንድ ጊዜ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ከጥቅማቸው ጉዳታቸው ሲበዛና ጤና-ቢስ የሆነ ሃሳብና ተግባራቸው ሲበዛ ዘወር ማለት የግድ ነው።
5. ለታላቅ እድል ለመዘጋጀት፦
አንዳንድ ጊዜ እስካሁን በሠራነው ሥራ፣ በሄድንበት መንገድና በድግግሞሹ የሕይወት ለውጥና እድገት ካላገኘን ራሳችንን ለማሻሻል የትኩረት ለውጥ ማድረግ ወሳኝ ነው።
በስልታዊ ማፈግፈግ ወቅት ምን ማድረግ አለብን?
ስልታዊ ማፈግፈግ ስናደርግ ከከባድ ሁኔታዎች በማምለጥ ዝም ብለን ገለል ማለት ሳይሆን የሚከተሉትን ልምምዶች ማዳበር ማለት ነው።
➢ ማሰላሰል (Reflect)፡ ምን ትምህርት ተምሬያለሁ?
➢ ማገገም (Recover)፡ አካላዊ፣ ስሜታዊ እና መንፈሳዊ ጥንካሬን መመለስ።
➢ እንደገና መገምገም (Re-evaluate)፡ ምን መቀጠል አለበት? ምን ማቆም አለበት?
➢ ቦታ መቀየር (Reposition)፡ ቀጣዩ ሥራዬ ወይም እድሌ የት ነው?
➢ እንደገና መገንባት (Rebuild)፡ አዳዲስ ልማዶችን፣ ሥርዓቶችን እና አመለካከቶችን ማዳበር።
አንዳንዴ ጥንካሬ የሚገኘው ዝም ብሎ ወደ ፊት በመገስገስ ሳይሆን መቼ ወደ ኋላ ማፈግፈግ እንዳለብን በማወቅ፣ በመረጋጋት፣ ጸሎት በማድረግ፣ አመለካከትን በማስተካከል እና ለቀጣዩ የሕይወት ምዕራፍ በመዘጋጀት ነው።
━━━━━━━━
📖 📖 📖 📖 📖
https://t.me/Ethiobooks
Telegram
ከስነ-ፅሁፍ ዓለም
✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል!
የቻናላችን https://t.me/Ethiobooks ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ።
ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ
@firaolbm እና
@tekletsadikK ተጠቀሙ።

7
3
1August 10, 2026 1.4K 7