እንደ ኦፊሺያላዊ መረጃ ከሆነ፦
🔍 563,960 ተማሪዎች ለመፈተን ተመዝገቡ
🔍 550,210 ተማሪዎች ፈተናውን ተፈተኑ
❔ፈተናውን አልፈው 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡት ግን 70,544 ብቻ ናቸው!
🚫 ይህ ማለት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ከሆኑት ተፈታኞች መካከል ከ87 በመቶ በላይ የሚሆኑት አብዛኞቹ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማምጣት አልቻሉም። ይህ ቁጥር ትልቅ እውነት ነው፤ ግን የሕይወት ማብቂያ አይደለም! 👇
1️⃣ የወረቀት ዘመን አብቅቷል፤ አሁን የሚሰራው "ክህሎት" ነው! 🛠
ለዓመታት ስንከተለው የነበረው አሮጌው የትምህርት ስርዓት ተቀይሯል። በዩኒቨርሲቲ ከ4 እስከ 7 ዓመታት አሳልፎ ዲግሪ ይዞ መውጣት ብቻውን ዋስትና የሆነበት ጊዜ አብቅቷል። ዛሬ ዓለም የምትፈልገው የወረቀት ባለቤቶችን ሳይሆን፣ ተጨባጭ ነገር መስራት የሚችሉ ሰዎችን ነው።
በየትኛውም መስክ ይሁኑ:- ቴክኖሎጂ፣ ንግድ፣ ግብርና፣ ጤና ወይም ፈጠራ,ኩባንያዎች እና ተቋማት የሚጠይቁት "ምን ዲግሪ አለህ?" ሳይሆን፣ "ምን መስራት ትችላለህ?" የሚለውን ነው።
2️⃣ የቴክኖሎጂ እና የዲጂታል ዘመን እውነታ 💻🚀
💡ዛሬ የምንኖርበት ዓለም ከቴክኖሎጂ ጋር የተሳሰረ ነው። ቴክኖሎጂን ከማንኛውም የሙያ ዘርፍ ጋር ማቀናጀት የቻለ ሰው አሸናፊ ነው።
💡ግራፊክ ዲዛይን፣ ዲጂታል ማርኬቲንግ፣ ኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ፣ የዳታ ትንተና፣ ወይም በየትኛውም ተመራጭ ዘርፍ ላይ አተኩረው መስራት ይችላሉ።
💡አሁን ላይ ከማንኛውም የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር በላይ 24 ሰዓት ከጎንዎ ሆኖ የሚያስተምርዎ፣ የሚመክርዎ እና ጥያቄዎችዎን የሚመልስልዎ ሰው ሰራሽ አስተዉሎት (AI) እና ዘመናዊ መሣሪያዎች በእጅዎ ላይ አሉ።
3️⃣ የ 6 ወር ቁርጠኝነት ሕይወትዎን ሊቀይር ይችላል! ⏳✨
💡ዩኒቨርሲት አልገባሁም ወይም ፈተና ወደኩ ብሎ ማዘን መፍትሄ አይደለም።
💡በምንወደው እና ባለን ፍላጎት ላይ ተመስርተን ቢያንስ ለ6 ወራት ሙሉ ትኩረት ሰጥተን ራሳችንን ስንፈትሽ እና አዲስ ክህሎት ስንማር ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንችላለን።
💡በራስዎ ጥረት (Self-taught) በመማር በቂ ልምድ ማከማቸት፣ በኦንላይን መስራት ወይም በዘርፉ ላይ በቀላሉ መቀጠር (Get hired) ይቻላል። ዓለም ዛሬ የምትፈልገው ታታሪዎችን እንጂ ወረቀት የያዙ ሰዎችን ብቻ አይደለም።
💡 ማጠቃለያ፡
ውጤቱ እንዳላሰባችሁት ሆኖ ተስፋ የቆረጣችሁ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን፤ ውጤቱ የወደፊት ዕጣ ፈንታችሁን ሊወስን አይችልም። እውነተኛው ስኬት ያለው በእጅዎ ባለው ክህሎት እና ባለው የትጋት መጠን ላይ ነው። ራሳችሁን አዘጋጁ፤ ቴክኖሎጂን ከሙያችሁ ጋር አስተሳስሩ፤ የወደፊቱን ዕጣ ፈንታ በራሳችሁ እጅ ቅረጹ! አትሰበሩ፣ ጸኑ! 💪🔥
✨ኢትዮ-አለርት✨
🔗 https://t.me/ethioalert
📢 @ethioalert
🤖 ለጥያቄዎች: @ethio_alerts_bot
🛡 ለወዳጅዎ ያጋሩ! 🛡
— Ethio Alert: Be Alert! —






