ሌሊት ፡- በባህረ ሐሳብ አቆጣጠር ሌሊቱና ቀኑ የተለያየ አቆጣጠር አላቸው፤ ሌሊትን ለማግኘት 3 ነገሮችን… — ባሕረ ሐሳብ (አቡሻኽር) አበበ ባዬ 📚 — TG.ME

✏️ ሌሊት ፡- በባህረ ሐሳብ አቆጣጠር ሌሊቱና ቀኑ የተለያየ አቆጣጠር አላቸው፤ ሌሊትን ለማግኘት 3 ነገሮችን እንደምራለን ፤

ሌሊት = አበቅቴ + ሠርቀ መዐልት + ሕጸጽ / 30
ምሳሌ 1፡- የ2018 ዓ.ም ሐምሌ 5 ሌሊቱን ለማወቅ ፥-

✏️ ሌሊት = 12 + 5 + 6 = 23 ስለዚህ የ2018 ዓ.ም ሐምሌ 5 ሌሊቱ 23 ነው የሚያድረው ማለት ነው፡፡ ይህም የ2019 ዓ.ም አበቅቴ ነው።

✏️ ጨረቃ (ሠርቀ ወርኅ) ደግሞ 27 ነው ማለት ነው፡፡ ሌሊቱ የሚያገለግለን የቤተክርስቲያን አገልግሎት ምንጊዜም ከሌሊቱ ስለሚጀምር ነው።

✏️ ጨረቃ (ሠርቀ ወርኅ - 4) ፡- ልደተ ጨረቃ ማለት ጨረቃ የወጣችበት ዕለት ማለት ነው። ይህም ከሌሊቱ ላይ 4 በመደመር ይገኛል 4 የጨረቃ ተውሳክ ነው፡፡ ኪ.ወ.ክ ገጽ 404

✏️ ሠርቀ ወርኅ (ልደተ ጨረቃ - 4) አወጣጡ

ፀሐይ ከጨረቃ የምታተርፈው 11 ዕለት ብቻ አይደለም፡፡ 22 ኬክሮስ፣ 1ካልዒት፣ 37 ሣልሲት፣52 ራብዒት፣ 48 ኃምሲት አለ፡፡ ድሜጥሮስ ግን አጽዋማት በዓላት የሚውሉባቸው ዕለታትንና አውራኅን በፀሐይ መንገድ ለማግኘት 11ዱን ዕለታት ብቻ አበቅቴ አደረገ፡፡ የቀሩትን አልሻቸውም፡፡ ኋላ ግን አቡሻኽር ሠርቀ ሌሊትና ልደተ ወርኅ ባይተካከልለት ከላይ የዘረዘርናቸውን ከኬክሮስ እስከ ኃምሲት ያሉትን አጠራቅሞ ዕለታት አገኘ ስማቸውንም ትራፋተ ዓውድ አላቸው፤ ከአውደ አበቅቴ የተረፉ ማለት ነው፡፡ እኒህ ዕለታት እስከ ዛሬ ድረስ አራት (4) ዕለታት ሁነዋል፡፡ እኒህን አራት ዕለታት ካልጨመሩ እውነተኛ ልደተ ወርኅና ሠርቀ ሌሊት አይገኙም፡፡ ስለዚህ ባለው አበቅቴ ላይ አራት መጨመር ግድ ነው፡፡ (መርሐ ዕውር ገጽ 7 (367)
❤4🙏1
July 11, 2026 803 3 3