ኢትዮ ቴሌኮም ለቴሌፕሌይ አሸናፊዎች የቢ.ዋይ.ዲ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ዕጣ የማውጣት መርኃ ግብር አካሄደ!… — Ethio telecom — TG.ME

ኢትዮ ቴሌኮም ለቴሌፕሌይ አሸናፊዎች የቢ.ዋይ.ዲ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ዕጣ የማውጣት መርኃ ግብር አካሄደ!

ኩባንያችን በዛሬው ዕለት በቴሌፕሌይ ዲጂታል ጨዋታ (tele Play) ያዘጋጀውን የሦስት ዘመናዊ የቢ.ዋይ.ዲ ኤሌክትሪክ መኪኖች የዕጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት በመስቀል አደባባይ አከናውኗል። የዕጣ አወጣጥ መርኃ ግብሩ የኩባንያችን ከፍተኛ አመራሮች፣ የብሔራዊ ሎተሪ አገልግሎት ተወካዮች፣ የሚዲያ አጋሮቻችን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተከናውኗል፡፡

ከነሐሴ 26 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ሲካሄድ በቆየው በዚህ የሽልማት መርኃ ግብር ዛሬ የወጡትን መኪኖች ሳይጨምር በአጠቃላይ ከ32.6 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ሽልማቶች ለደንበኞች ተበርክተዋል።
ከእነዚህም መካከል፦
📱 119 ዘመናዊ ስማርት ስልኮች፣
💸 17.76 ሚሊዮን ብር የቴሌብር ኤሌክትሮኒክ ገንዘብ፣
✈️ ለ17 ደንበኞች የሀገር ውስጥ የጉዞ ዕድል፣
🎁 1.9 ሚሊዮን የሞባይል ጥቅሎች ይገኙበታል።

ለዛሬዎቹ ዕድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን፣ ሽልማታቸውን በቅርቡ በሚዘጋጅ ሥነ ሥርዓት በይፋ የምናስረክብ ይሆናል።

የቴሌፕሌይ የሽልማትና የመዝናኛ መርኃ ግብር በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ ደንበኞች በቀጣይም በቴሌ ፕሌይ በመጫወት የኤሌክትሪክ መኪኖችን ጨምሮ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን የማሸነፍ ዕድላችሁን እንድትሞክሩ እንጋብዛለን።

ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/45Uzlw0

#telePlay
#Ethiotelecom #telebirr #telebirrSuperApp #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #RealizingDigitalEthiopia
❤48👍13😁7👏4🆒3
August 29, 2026 12.8K 4