አሜሪካ የተቃወመችው የአፍሪካን ትክክለኛ የቆዳ ስፋት የሚያሳይ አዲስ ካርታ በተባበሩት መንግሥታት ፀደቀ… — ETHIO-MEREJA® — TG.ME

አሜሪካ የተቃወመችው የአፍሪካን ትክክለኛ የቆዳ ስፋት የሚያሳይ አዲስ ካርታ በተባበሩት መንግሥታት ፀደቀ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ፣ የተለመደው የዓለም ካርታ የአፍሪካን የቆዳ ስፋት ይበልጥ ትክክለኛ በሆነ መጠን እንዲቀመጥ በሚያደርግ አዲስ ካርታ እንዲተካ ወሰነ።

በቶጎ አቅራቢነት እና በአፍሪካ ኅብረት አባል አገራት ድጋፍ የቀረበው ይህ 'ኮሬክት ዘ ማፕ' የተሰኘው የውሳኔ ሃሳብ፣ ፈረንሳይ እና ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ 164 አገራት ድጋፍ ሰጥተውት ፀድቋል።
አሜሪካ ውሳኔውን የተቃወመች ብቸኛ አገር ስትሆን፣ ስድስት አገራት ደግሞ ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል።

ይህ የተመድ ውሳኔ አስገዳጅ አይደለም። ይሁን እንጂ ባይሆንም፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ተቋማት የሚጠቀሙባቸውን ካርታዎች እንደሚቀይር ይጠበቃል።
አሁን ያለው የ'መርኬተር' ካርታ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፣ ከ16ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በስፋት ጥቅም ላይ ውሏል።በዚህ ካርታ ላይ በስፋት 14 እጥፍ የምትበልጠውን አፍሪካን ከግሪንላንድ ጋር በእኩል መጠን በማስቀመጡ ከፍተኛ ትችት ሲቀርብበት ቆይቷል።

ይህ መሆኑ የምድር ወገብ አካባቢ የሚገኙ አገራት የልማት ፍላጎት እና አቅምን አሳንሶ እንዲታይ ማድረጉን ተቺዎች ይናገራሉ።
የመርኬተር ካርታ በአውሮፓውያኑ 1569 የተነደፈው በቤልጂዬማዊው የካርታ ባለሙያ ጄራርደስ መርኬተር ነው። ካርታው የተሠራውም አውሮፓውያን አሳሾች በዓለም ዙሪያ ለሚያደርጉት ጉዞ እገዛ ለማቅረብ ነበር። (BBC Amharic)



      -ETHIO-MEREJA-
     T.me/ethio_mereja
❤26👏6
September 5, 2026 6.9K 4 8