የብሔራዊ ባንክ ማሳሰቢያ!! የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለሕዝቡ፣ ለዲያስፖራውና ለመላው የገንዘብ ተጠቃሚ ጠንካራ… — ETHIO-MEREJA® — TG.ME

የብሔራዊ ባንክ ማሳሰቢያ!!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለሕዝቡ፣ ለዲያስፖራውና ለመላው የገንዘብ ተጠቃሚ ጠንካራ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

ሕገወጥ የሃዋላ አውታረ መረቦችንና ፈቃድ ያልተሰጣቸውን የገንዘብ ማስተላለፊያ ወኪሎች መጠቀም ከፍተኛ የፋይናንስና የሕግ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ባንኩ አስጠንቅቋል።

ገንዘብዎ ደህንነት ይገባዋል! በሕገወጥ መንገድ ገንዘብ መላክ ወይም መቀበል የገንዘብ ኪሳራ፣ የክፍያ መዘግየት፣ የሂሳብ መገደብ እና ሕጋዊ እርምጃ ሊያስከትል ይችላል።

በተለይ በዚህ ወቅት የገንዘብ ልውውጥ መጠን እየጨመረ በመሆኑ፣ ደንበኞች፣ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላትና መላው ሕዝብ ገንዘብ ሲልኩም ሆነ ሲቀበሉ በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የተሰጣቸውን ሕጋዊ የገንዘብ ማስተላለፊያ አማራጮች ብቻ እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።

ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የሌላቸው ተብለው የተጠቀሱ የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶች፦

1. Adulis Money Transfer (ADZ)
2. Amal Express
3. Amal USA
4. Amana Express
5. Avanti
6. Awash Direct
7. Bakaal Money Transfer
8. Jubba Express
9. Rasmy Pay
10. Ramad Pay / Ramada Pay (Kaah)
11. Shgey Money Transfer
12. Taaj Financial Service
13. Tasa Pay
14. Tawakal Money Services
15. USwyre
16. World Direct Link
17. Zola ናቸው።


      -ETHIO-MEREJA-
     T.me/ethio_mereja
❤41😢2
August 29, 2026 9.1K 33