ታሪካዊ የቤት መግዣ ብድር ማዕቀፍ ሊቋቋም ነው በሀገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያው የሆነውን የተለየ የቤት መግዣ… — Ethiopian Construction Vacancy & Tender — TG.ME

ታሪካዊ የቤት መግዣ ብድር ማዕቀፍ ሊቋቋም ነ

በሀገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያው የሆነውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችል ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል ዛሬ መፈረሙ ተገለጸ።

በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመው ይህ አዲስ ተቋም፤ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅኦ የሚያደርግበት መሆኑ ተመላክቷል።

ተቋሙ በባንክ ዘርፉ ውስጥ የሚታየውን የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠን የሚቀርፍ እና በመላው ሀገሪቱ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስ እንደሚያስገኝ ተነግሯል።

ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ እንዲሁም በፋይናንስ ሥርዓቱ ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ወሳኝ እርምጃ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

በቀጣይነትም ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገልጿል።

@etconp
👍7❤2
September 3, 2026 1.5K 3