በግንባታ ቦታ ላይ የምንጠቀማቸው የሪባር (Rebar) ብረቶች ላይ የተፃፉት ፊደላትና ቁጥሮች የብረቱን ጥንካሬ፣ የመታጠፍ አቅም እና የምህንድስና ስታንዳርድ ይነግሩናል።
🌟የ B500DWR ትርጉም በዝርዝር፦
- B (Reinforcing Steel): ለኮንክሪት ማጠናከሪያነት የሚያገለግል የስትራክቸር ብረት መሆኑን ያሳያል።
- 500 (Yield Strength): የብረቱ የመሸከም አቅም ወይም Yield Strength 500 MPa መሆኑን ይገልፃል።
- D (Ductility Class D): ከፍተኛ የመታጠፍና የመለጠጥ አቅም (High Ductility) ያለው መሆኑን ያሳያል። በተለይም የመሬት መንቀጥቀጥን (Seismic Load) ለመቋቋም ለሚሰሩ ህንፃዎች ተመራጭ ነው።
- W (Weldable): ብረቱ በቀላሉ የሚበየድ (Weld የሚደረግ) እና በብየዳ ወቅት ጥንካሬውን የማይጣጣ መሆኑን ያመለክታል።
- R (Ribbed Bar): ከኮንክሪት ጋር በጥሩ ሁኔታ እንዲጣበቅ (Bonding) ተደርጎ በካራ የተሰራ (Deformed Bar) መሆኑን ያሳያል።
በእናንተ ሳይት ላይ አብዛኛውን ጊዜ የትኛውን የብረት ግሬድ (Grade) ታወጣላችሁ?
@etconp



