የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ መገደላቸውንና አስከሬናቸውም መገኘቱን አንድ ከፍተኛ የእስራኤል…

የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ መገደላቸውንና አስከሬናቸውም መገኘቱን አንድ ከፍተኛ የእስራኤል ባለሥልጣን ለሮይተርስ ዜና ወኪል ገለጹ።

እስካሁን ድረስ ከኢራን በኩል የተሰጠ ይፋዊ ማረጋገጫ የለም።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በሰጡት መግለጫ ደግሞ ፣ አያቶላ ኻሜኒ በእስራኤልና በአሜሪካ የአየር ጥቃት መገደላቸውን የሚያሳዩ በርካታ ምልክቶች መኖራቸውን ገልጸዋል።

“ዛሬ ማለዳ የአምባገነኑን ኻሜኒ ቅጥር ግቢ ደምስሰናል፤ ይህ አምባገነን ከእንግዲህ የሌለ መሆኑን የሚያሳዩ ብዙ ምልክቶች አሉ “ ሲሉ ተደምጠዋል።

ከኻሜኒ በተጨማሪ የገዥው ሥርዓት ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የኢራን አብዮታዊ ዘበብ (RGC) አዛዦች እና የኑክሌር ፕሮግራም ቁልፍ ሰዎች መገደላቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

“ እስራኤል በቀጣይ ቀናትም በሺዎች የሚቆጠሩ የሽብር ሥርዓቱ ኢላማዎች ላይ ጥቃቷን ትቀጥላለች “ ሲሉ አስታውቀዋል።

በቴህራን የሚገኘው የኻሜኒ መኖሪያ ግቢ ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰበት የሳተላይት ምስሎች ሲወጡ ውለዋል።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩላቸው መሪው “ ደህና ናቸው “ የሚል መግለጫ ቢሰጡም እስካሁን ኻሜኒ በአካል ታይተው መግለጫ አልሰጡም።
March 1, 2026 1.2K