በ11 የስፖርት አይነቶች ተለይቶ ለሁለት ወራት ለልጆች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና መቋጫውን አግኝቷል ።
በአራት ኪሎ የስፖርት ትምህርትና ሰልጠና ማዕከል በክረምቱ በ11 የስፖርት አይነቶች ለልጆች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና 603 ሰልጣኞችን በማስመረቅ ተጠናቋል ።
ይህ ስልጠና ብቃት ያላቸውን ስፖርተኞች ለበጋው መደበኛ ስልጠና ለመለየት፣ እንዲሁም ንቁና ብቁ ዜጋን ለመፍጠር የተደረገ መሆኑንም የማእከሉ ስራአስኪያጅ አቶ ሃይሉ ግርማ ለጣቢያችን ተናግረዋል ።
በዚህም የጠረጴዛ ቴኒስ፣ቴኳንዶ፣ የእጅ ኳስ እና የቅርጫት ኳስ ስልጠናን ጨምሮ በ11 የስፖርት አይነቶች በሁለቱም ፆታዎች ለ603 ልጆች ስልጠና መስጠት መቻሉን ገልጸዋል ።
አክለው እንዲህ አይነት ስልጠናዎች ልጆች ለበጋው የትምህርት ጊዜ እንዲዘጋጁ እና በመልካም ስነምግባር እንዲቀረፁ ለማድረግ ትልቅ መሣሪያ ነው ያሉት ስራአስኪያጁ የሰልጣኞቹ ቤተሰቦች ከጎናቸው እንደነበሩም ተናግረዋል ።
ቤተሰቦቻቸውም ከጎናችን በነበሩበት በዚህ ስልጠና ከ603 ሰልጣኞች መካከል በየስፖርት አይነቱ አቅሙ ያላቸው 246 ወጣቶችን ለመደበኛ ቋሚ ስልጠናው ለይተው ማውጣት መቻላቸውን ገልጸዋል ።
Era Journal !!

September 18, 2026 17