ጰራቅሊጦስ መንፈስቅዱስ(παράκλητος) ጰራቅሊጦስ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የአንዱ አምላክ እግዚአብሔር… — ሐመረ ኖኅ ሚዲያ — TG.ME

ጰራቅሊጦስ

መንፈስቅዱስ(παράκλητος)

ጰራቅሊጦስ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የአንዱ አምላክ እግዚአብሔር ሦስተኛው አካል(person )ነው።
መንፈስቅዱስ በባህሪው መንጽዔ(የሚያጸና) እና መንጽሒ(የሚያነጻ) ሲሆን ለእግዚአብሔር ሥላሴ እስትንፋሳቸው ነው። እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ አንድም ከሳቴ ምስጢር ወይንም ምስጢር ገላጭ በመባል ይጠራል።
መንፈስቅዱስ የእግዚአብሔር እስትንፋስ (ህይወት )ነው። በአብና በወልድ ውስጥ ህልው ሆኖ ይኖራል።
Holly sprit is also called peraclitos and
he is the third person of the one the Almighty God
መንፈስቅዱስ ኀያል እግዚአብሔር በመሆኑ የእግዚአብሔር ነገር መመርመር የሚችል ብቸኛ ነው።
መንፈስ ቅዱስ ብዙ መጠሪያዎች አሉት ከነዚህም መካከል
፩.መንጽሒ (የሚያነጻ)ሲሆን ሰዎችን ከኀጢአት ጠብቆ የሚያነጻ ብሎም ሰዎች በኀጢአት ከ ወደቁ በኋላ ንስሐ ሲገቡ በልባቸው ታትሞ ይቅር በማለት ያነጻቸዋል።
፪.መጽንዒ(የሚያጸና) በሁኔታዎች በችግሮችና በተግዳሮቶች ውስጥ ሰዎችን አጽንቶ እግዚአብሔርን እንዳይክዱና በምልአት እንዲገልጡት የሚረዳቸው ነው።
፫.ከሳቴ ምስጢር(ምስጢርን የሚገልጥ)
ከእግዚአብሔር የሆነውን ምስጢር እውቀት እንደ ፈቃደ እግዚአብሔር ይገልጣል። ሰዎችም በዚህ መንፈስ ተነሳስተው ትንቢትን ይናገራሉ።
፬.ናዛዚ(የሚያረጋጋ) የሚያጽናና ነው
“እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።”
— ዮሐንስ 16፥7
፭.መስተስርይ (ይቅር ባይ)ፍጹም አምላክ በመሆኑ ኀጢአትን ሁሉ ይቅር ይላል።
በዓለ ጰራቅሊጦስ የተለያዩ አይነት ስያሜዎች አሉት እነርሱም
በዓለ ጰራቅሊጦስ
በዓለ ጰንጠቆስጤ (50ቀን)
በዓለ ሀምሳ
በዓለ ሰዊት(የአይሁድ በዓል የነበረ)በዚያን እለት የሚከበር
መንፈስቅዱስ በሐዋርያት መካከል ጌታ ኢየሱስ ካረገ ከ 10ቀን በኋላ በመካከላቸው በእሳትና በነፋስ አምሳል ተገለጠ። የመንግስትን ወንጌል እንዲያስፋፉ 72 ቋንቋዎች ተገለጡላቸው። በዕለቱም በ ረድኤት ወ በ ኀይለ መንፈስ ቅዱስ በመክበራቸው በስብከት 3000 ምዕመናንን ለጌታ ጨምረዋል።
መንፈስቅዱስ አንድ የህይወት ምንጭ ሲሆን የተለያየ ጸጋ ለሰዎች ይሰጣል ።
ሐዋርያት በዚህ ቅዱስ መንፈስ ከከበሩ በኋላ ወደ ጾም ገቡ አለምንም በወንጌል ማጥለቅለቅ ጀምረው እስከ ፍጸሜያቸው ድረስ አድርገውታል።
እግዚአብሔር መንፈስቅዱስ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለ የነበረ የሚኖረውም እርሱ ከአብና ከ ወልድ ጋር እርሱ ነው።
ክብርና አምልኮ ውዳሴ ከምድር እስከ አርያም ድረስ ለእርሱ ለመንፈስቅዱስ

ይሁን።

አሜን

ዲያቆን የኋላሸት

ባህርዳር


2015 ዓ.ም
Glory to the Hollysprit

እንኳን አደረሰን
❤8
May 30, 2026 965