እንኳን ለብርሃነ ደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ❕ ​ደብረ ታቦር ምን ማለት ነው❔ "ደብረ… — EOTC መጻሕፍት — TG.ME

☦️☦️ ☦️☦️ ☦️☦️🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ​እንኳን ለብርሃነ ደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ❕ ​ደብረ ታቦር ምን ማለት ነው❔ "ደብረ ታቦር" ማለት የታቦር ተራራ ማለት ሲሆን፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚሁ ተራራ ላይ ለደቀ መዛሙርቱ ምስጢረ መለኮቱን (ብርሃነ መለኮቱን) የገለጠበት ታላቅ አበይት ከሚባሉት ዘጠኙ የጌታ በዓላት አንዱ ነው። ​ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው❔ "ቡሄ" ማለት ቦሄ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን "ብርሃን፣ ጽሁ፣ ደማቅ" ማለት ነው። ጌታችን በታቦር ተራራ ላይ የተገለጠበትን መለኮታዊ ብርሃን የሚያስታውስ ነው (ማቴ. 17፡1-9)። በተጨማሪም "ቡሄ" ማለት የክረምቱ ጨለማ አልፎ የብርሃንና የደስታ ጊዜ መቃረቡን የሚያበስር በዓል ነው። ​የችቦው ምስጢር፦ በታቦር ተራራ ላይ የታየውን መለኮታዊ ብርሃን ለማሰብ ነው። ​የሙልሙል ዳቦው ምስጢር፦ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ተራራው ሲወጡ እናቶቻቸው ስንቅ አዘጋጅተው የላኩላቸውን የፍቅርና የእንግዳ ተቀባይነት ባህል ለማሰብ ነው። ​አምላካችን እግዚአብሔር የበዓሉን በረከትና ረድኤት ለሁላችንም ያብዛልን፤ በሃይማኖትና በምግባር አጽንቶ በሰላም ያቆየን❕ ​🕯መልካም የደብረ ታቦር በዓል❕ ​💡 ለወዳጆቻችሁ Share አድርጉት❕ Like (👍🙏❤️) ማድረጋችሁንም አትርሱ❕   ​❖═ @OrthodoxTewahedoTrue ═❖ ❖══ @OrthodoxTewahedoTrue ══❖    ❖═ @OrthodoxTewahedoTrue ═❖

August 18, 2026 7.5K 37