የኢትዮጵያው አግሪቴክ ኩባንያ Lersha አህጉራዊውን የ Africa Sustainable Futures ሽልማት አሸነፈ
በ Financial Times እና በዓለም ባንክ ግሩፕ አባል MIGA በጋራ በተዘጋጀው የ 2026 Africa Sustainable Futures Awards ውድድር ላይ የኢትዮጵያው አግሪቴክ ኩባንያ Lersha ከፍተኛውን የአሸናፊነት ማዕረግ ተጎናጸፈ። ኩባንያው በመላው አፍሪካ ከቀረቡ ወደ 600 የሚጠጉ ተወዳዳሪ ፕሮጀክቶች መካከል የዓመቱ የላቀ ስኬት (Judges' Award for Excellence) እና የግብርና ቢዝነስ (Agribusiness Award) አሸናፊ በመሆን ሁለት አህጉራዊ ሽልማቶችን ተቀናጅቷል።
በ Green Agro Solution PLC የበለፀገው Lersha አነስተኛ አርሶ አደሮችን ከፋይናንስ፣ ከሰብል ኢንሹራንስ፣ ከግብርና ግብአቶች እና ከገበያ እድሎች ጋር የሚያገናኝ የዲጂታል መድረክ ነው። በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ኡጋንዳ የሚንቀሳቀሰው ይህ ፕላትፎርም በ GSMA መረጃ መሠረት ከ 620 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን አገልግሎት መስጠት የቻለ ሲሆን፣ ከ 76 ሺህ በላይ የሚሆኑት የፋይናንስ ብድር አግኝተዋል። ኩባንያው ከሞባይል መተግበሪያ በተጨማሪ ከ 2,500 በላይ የአካባቢ ወኪሎችን በመጠቀም ስማርትፎን የሌላቸውን አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ያደርጋል።
🔗 Birr Metrics
#Agritech #Ethiopia #Startups

Birr Metrics
Ethiopian Agritech Firm Lersha Wins Top Africa Award
The Ethiopian-founded agricultural technology company secured both the overall excellence award and the agribusiness prize at a continental competition
October 24, 2026 15