ዛምዛም ባንክ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ
የመጀመሪያው ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ሰጪ የሆነው ዛምዛም ባንክ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከታክስ እና ተጠባባቂ ክፍያዎች በፊት 1.8 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን ይፋ አደረገ። የባንኩ የተጣራ ትርፍ ለመጀመሪያ ጊዜ 1 ቢሊዮን ብር ማለፉ የተገለፀ ሲሆን፡ አጠቃላይ የቁጠባ ተቀማጭ ገንዘቡም 20.4 ቢሊዮን ብር በመድረስ የታቀደውን 144 በመቶ ማሳካት ችሏል። በተጨማሪም የባንኩ አጠቃላይ የሀብት መጠን 29.24 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፡ የደንበኞቹ ቁጥር ደግሞ በ144 በመቶ እድገት በማሳየት ከ973 ሺህ በላይ ማድረስ ተችሏል።
ይህ ከፍተኛ አፈፃፀም የተመዘገበው ባንኩ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እና መሰረተ ልማት ላይ ባደረገው ሰፊ ኢንቨስትመንት ምክንያት እንደሆነ ተገልፀዋል። በዚህም የዲጂታል ባንክ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ150 በመቶ በላይ ያደገ ሲሆን፡ አብዛኞቹ የባንኩ የፋይናንስ ግብይቶች በዲጂታል መስመሮች የሚከናወኑ ሆነዋል። በተጨማሪም ባንኩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለባንኮች ያስቀመጠውን የ5 ቢሊዮን ብር አነስተኛ የተከፈለ ካፒታል መስፈርት ከሰኔ 2026 የጊዜ ገደብ አስቀድሞ ማሟላቱን አስታውቋል።
🔗 Birr Metrics
#Banking #Ethiopia #Fintech

Birr Metrics
Zamzam Bank Posts 1.8 Billion Birr Pre-Tax Profit as Deposit
Net profit tops 1 billion Birr for the first time, customer base grows 144 percent to over 973,000, digital users rise more than 150 percent, and capital now
October 25, 2026 16