በሰሜናዊ ናይጄሪያ የ TikTok አገልግሎት ከተቋረጠ ከአንድ ወር በላይ ተቆጠረ
በሰሜናዊ ናይጄሪያ በሚገኙ እንደ ካኖ፣ ካዱና፣ ሶኮቶ እና ጎምቤ ባሉ በርካታ ግዛቶች የ TikTok አገልግሎት ከተቋረጠ ከአንድ ወር በላይ እንደሆደው ተገለጸ። በተለይም የ MTN እና Airtel የሞባይል ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች መተግበሪያውን በቀጥታ ማግኘት ባለመቻላቸው ወደ VPN እና ሌሎች የኢንተርኔት አማራጮች ለማዘንበል ተገደዋል። በናይጄሪያ ከ47.8 ሚሊዮን በላይ የ TikTok ተጠቃሚዎች እና ከ6.3 ሚሊዮን በላይ ይዘት ፈጣሪዎች የሚገኙ ሲሆን፣ አገልግሎቱ መቋረጡ በዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች እና በኦንላይን ንግዶች ገቢ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ ይገኛል።
የቲክቶክ ባለቤት የሆነው ኩባንያ ችግሩ ከእሱ መተግበሪያ ጋር እንደማይያያዝ ቢገልጽም፣ የናይጄሪያ መንግሥት እና የቴሌኮም ኦፕሬተሮች እስካሁን ምንም ዓይነት ምላሽ አልሰጡም። የመብት ተሟጋች እና የሲቪል ማህበራት በበኩላቸው ድርጊቱ እ.ኤ.አ. በ2027 ከሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ በፊት የዜጎችን የዲጂታል መብት የሚያስከፋ እና ሆን ተብሎ የተደረገ የኢንተርኔት ፍጥነት ቅነሳ ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
🔗 Connecting Africa
#TikTok #Nigeria #InternetAccess
Connecting Africa
TikTok blackout hits northern parts of Nigeria
TikTok users in the northern states of Nigeria have been struggling to access their accounts for over a month, unbeknown to the government and TikTok.

October 21, 2026 10