ያልተፈቀዱ የ AI መሳሪያዎች አጠቃቀም የሳይበር ደህንነት ስጋት ደቅኗል ተባለ
የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች እና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ተቋማት ሳይፈቅዱ እና ሳይቆጣጠሩ በሰራተኞች የሚደረግ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አጠቃቀም ወይም "shadow AI" ከፍተኛ የመረጃ ደህንነት ስጋት ደቅኗል ሲሉ አስጠነቀቁ። Sophos ያቀረበው የ Gartner ጥናት እንደሚያሳየው 69 በመቶ የሚሆኑ የሳይበር ደህንነት መሪዎች ሰራተኞቻቸው ያልተፈቀዱ የ AI ኤጀንቶችን እና መሳሪያዎችን ይጠቀማሉ ብለው እንደሚጠረጥሩ ወይም በቂ ማስረጃ እንዳላቸው ገልጸዋል። በተጨማሪም Kaspersky ባወጣው መረጃ በ2026 የመጀመሪያው መንፈቅ በ AI አገልግሎቶች ላይ የተመዘገቡ የደህንነት ክፍተቶች በአስር እጥፍ ማደጋቸውን አመልክቷል።
ያልተገደበ የ AI አጠቃቀም ተቋማት የውስጥ ምስጢራዊ መረጃዎቻቸውን እና የምንጭ ኮዶቻቸውን ለአደጋ እንዲያጋልጡ ያደርጋቸዋል። ለምሳሌ ያህል Samsung እ.ኤ.አ. በ2023 ኢንጂነሮቹ ምስጢራዊ የውስጥ ኮዶችን እና የስብሰባ ማስታወሻዎችን ወደ ChatGPT በመጫናቸው ምክንያት የ GenAI መሳሪያዎች አጠቃቀምን በጊዜያዊነት ለማገድ ተገዶ ነበር። የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች እንደሚያስረዱት ኩባንያዎች ይህንን ስጋት ለመቀነስና ለመቆጣጠር ለሰራተኞቻቸው የተቋሙ የደህንነትና የመታወቂያ ቁጥጥር የተዘረጋላቸውን አማራጭ የ AI መሳሪያዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
🔗 ITWeb Africa
#AI #Cybersecurity #Tech
ITWeb
Shadow AI a growing concern, warn cyber security experts
Cyber security experts underline the need for vigilance as AI adoption remains a dominant focus among organisations.

October 20, 2026 17