በኬንያ የሞባይል ገንዘብ ተመዝጋቢዎች ቁጥር 95.31 ሚሊዮን ደረሰ
በኬንያ የሞባይል ገንዘብ ተመዝጋቢዎች ቁጥር 95.31 ሚሊዮን መድረሱን የቅርብ ጊዜ መረጃዎች አመላከቱ። እስከ ኦገስት 2026 ባለው አንድ ዓመት ውስጥ ብቻ 7.85 ሚሊዮን አዳዲስ ተመዝጋቢዎች የተቀላቀሉ ሲሆን፣ የወርሃዊ የገንዘብ ዝውውር መጠን 5.90 ቢሊዮን USD ደርሷል። የ M-PESA አገልግሎት የገበያውን 88.8 በመቶ ድርሻ በመያዝ አሁንም የበላይነቱን የቀጠለ ሲሆን፣ የዲጂታል ክፍያዎች መስፋፋት ግን የኤጀንቶችን ቁጥር እንዲቀንስ አድርጓል። በአንፃሩ በኢትዮጵያ Telebirr 58.61 ሚሊዮን እንዲሁም Safaricom M-Pesa 5.2 ሚሊዮን ተመዝጋቢዎችን ማፍራት ችለዋል።
በኬንያ የሞባይል ገንዘብ ተዳራሽነት 84 በመቶ ቢደርስም፣ በFinAccess ጥናት መሰረት የህዝቡ የፋይናንስ ጤናማነት ከ39.4 በመቶ ወደ 18.3 በመቶ ዝቅ ብሏል። ይህም የዲጂታል ብድር እና አገልግሎቶች መስፋፋት ተጠቃሚዎችን ለፋይናንስ ችግር መዳረጉን አመላካች ነው። በመሆኑም ኬንያ ከ2025 እስከ 2028 በሚተገበረው አዲስ የፋይናንስ አካታችነት ስትራቴጂ ትኩረቷን ከአገልግሎት ተዳራሽነት ማሳደግ ባሻገር የዜጎችን የፋይናንስ ጤናማነት፣ ቁጠባ እና የደንበኞች ጥበቃ ወደ ማጠናከር አዙራለች።
🔗 Birr Metrics
#Fintech #Kenya #MobileMoney

Birr Metrics
Kenya's Mobile Money Base Reaches 95.31 Million as FinAccess
Subscriptions have hit a record high on continued M-PESA expansion, but survey data shows the share of financially healthy adults has fallen to 18.3 percent,
October 20, 2026 20