የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ለ8 ዋስትናዎች የ OTC የንግድ መድረክ ሊጀምር ነው የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ (ESX) ለዋናው የኮርፖሬት መመዘኛ የማያሟሉ ወይም አማራጭ የንግድ መንገድ ለሚመርጡ ስምንት ዋስትናዎች (securities) ከስቶክ ኤክስቼንጅ ውጭ የሚከናወን የ OTC (Over-the-Counter) የንግድ መድረክ በማዘጋጀት ላይ መሆኑን የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዮዲት ካሳ አስታወቁ። በአሁኑ ወቅት በዋናው የገበያ መድረክ ላይ የቴሌኮም እና የባንክ አክሲዮኖችን ጨምሮ ሰባት ዋስትናዎች በንቃት እየተገበያዩ ይገኛሉ። ይህ አዲስ የ OTC አሰራር በልማት ላይ ላለው የሀገሪቱ የሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ የኩባንያዎችን እና የባለሀብቶችን ተሳትፎ በከፍተኛ ሁኔታ ለማስፋፋት ያለመ ነው። በተጨማሪም ESX በሁለተኛ ደረጃ ገበያ ላይ የመንግሥት የቴዥሪ ቢሎችን ንግድ ለማሳደግ እና የረጅም ጊዜ የብድር ሰነዶች ገበያን ለማጎልበት እየሰራ ሲሆን፡ በአሁኑ ወቅት የኢንቨስትመንት ባንኮችን እና ደላሎችን ጨምሮ ዘጠኝ የተመዘገቡ አባላት እና እስከ 25 የሚደርሱ ፍቃድ ያላቸው ተቋማት ገበያውን በመደገፍ ላይ ይገኛሉ። 🔗 Capital Ethiopia #ESX #Ethiopia #CapitalMarket
October 28, 2026 22