የኬንያ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ከአሜሪካ ጋር የተደረገውን የጤና ስምምነት እገዳ አነሳ
የኬንያ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በህመምተኞች የግል የጤና መረጃ ደህንነት ስጋት ምክንያት በ High Court ታግዶ የነበረውን የኬንያ እና አሜሪካ የጤና ትብብር ስምምነት ትግበራ እንዲቀጥል ውሳኔ አስተላለፈ። አምስት ዓመታት የሚቆየው እና 1.6 ቢሊዮን USD ወይም 207 ቢሊዮን KSh በጀት የተመደበለት ይህ ፕሮግራም መታገዱ፣ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የኤችአይቪ፣ የቲቢ እና የወባ ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚዎችን እንደሚጎዳ ፍርድ ቤቱ ገልጿል።
የ COFEK ድርጅት እና ሴናተር Okiya Omtatah ያቀረቡት አቤቱታ የስምምነቱ የህክምና መረጃ ልውውጥ ደንብ የዜጎችን የግል መረጃ ደህንነት እና ህገ-መንግስታዊ መብት ይጥሳል የሚል ነው። ፍርድ ቤቱ የጤና አገልግሎቱን ቀጣይነት በማስቀደሙ መንግስት የዲጂታል ጤና ስርዓቶችን እና የበሽታ መከታተያ መሰረተ ልማቶችን እንዲተገብር መንገድ የከፈተ ሲሆን፣ የመረጃ ጥበቃን በተመለከተ የተነሳው የህግ ክርክር ግን በፍርድ ቤቱ ይቀጥላል።
🔗 TechTrends KE
#DataPrivacy #Kenya #DigitalHealth

TechTrendsKE
Court of Appeal allows Kenya-US health deal to proceed despite privacy challenge
Kenya can proceed with its US health cooperation framework after the Court of Appeal lifted the suspension. Questions over patient data, constitutional compliance and oversight remain central to the legal challenge.
October 14, 2026 39