Africa Bitcoin Corporation አራት የቦርድ ዳይሬክተሮች በመልቀቃቸው የቦርድ ውዝግብ ውስጥ ገባ
በደቡብ አፍሪካ የጆሃንስበርግ አክሲዮን ገበያ የተመዘገበው የቢትኮይን ግምጃ ቤት እና የፋይናንስ አገልግሎት ኩባንያ Africa Bitcoin Corporation (ABC) በባለአክሲዮኖች እና በቦርዱ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ሳቢያ አራት የቦርድ ዳይሬክተሮች ከኃላፊነታቸው ለቀቁ። ከስራ ከለቀቁት አመራሮች መካከል የቦርዱ ሰብሳቢ Norma Sephuma እና ጊዜያዊ ዋና ሥራ አስፈጻሚ Stafford Masie ይገኙበታል። የዳይሬክተሮቹ መልቀቅ የተከሰተው 71.8 በመቶ የሚሆን የኩባንያው ድርሻ ያላቸው ባለአክሲዮኖች ዳይሬክተሮቹ እንዲነሱ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከተሎ ሲሆን፡ በአሁኑ ወቅት በኩባንያው ቦርድ ውስጥ ሁለት ዳይሬክተሮች ብቻ ቀርተዋል።
ይህ የቦርድ ውዝግብ የተከሰተው ኩባንያው ከአነስተኛና መካከለኛ ንግዶች አበዳሪነት ወደ ቢትኮይን ግምጃ ቤት ኩባንያነት በሚያደርገው ሽግግር ወቅት ነው። ቀደም ሲል Altvest Capital ተብሎ የሚጠራው ይህ ኩባንያ፡ በቅርቡ የደቡብ አፍሪካ የፋይናንስ ዘርፍ ተቆጣጣሪ (FSCA) በቀድሞ ዋና ሥራ አስፈጻሚ Warren Wheatley እና ሌሎች ሁለት አመራሮች ላይ የአክሲዮን ዋጋ ማጭበርበር ፈጽመዋል በሚል የ9 ሚሊዮን ራንድ (546 ሺህ USD) መቀጮ እና የ20 ዓመታት የሙያ እገዳ ጥሎባቸዋል።
🔗 TechCabal
#Fintech #Bitcoin #SouthAfrica

TechCabal
Shareholder revolt leaves Africa Bitcoin Corporation with two directors
Africa Bitcoin Corporation is left with two directors after four resign amid a shareholder dispute over board appointments and regulatory scrutiny.
October 13, 2026 37