GSMA የ 5G ኢንቨስትመንት፣ የ 6G እና የዲጂታል ተደራሽነት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አቅጣጫዎች ይፋ አደረገ
የአለም አቀፉ የቴሌኮም ድርጅት GSMA የቦርድ አባላት በህንድ ኒው ዴሊ ባካሄዱት ስብሰባ ለአለም አቀፍ የሞባይል ኔትወርክ ዕድገት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል። ድርጅቱ እንዳስታወቀው በ 2025 የሞባይል ቴክኖሎጂዎችና አገልግሎቶች ለአለም ኢኮኖሚ 6 ትሪሊዮን USD አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሲሆን፣ ይህም እስከ 2030 ድረስ ወደ 11.3 ትሪሊዮን USD ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም የቴሌኮም ኦፐሬተሮች ከ 2025 እስከ 2030 ባለው ጊዜ ውስጥ ለኔትወርክ ማስፋፊያ እና ማሻሻያ 1.2 ትሪሊዮን USD የካፒታል ወጪ ያደርጋሉ። በ 2030 ከጠቅላላው የሞባይል ግንኙነቶች 57 በመቶው በ 5G ኔትወርክ ላይ እንደሚሆን ተገልጿል።
በስብሰባው ላይ የዲጂታል ተደራሽነት ልዩነትን ማጥበብ ዋነኛ ትኩረት የነበረ ሲሆን፣ በአለም አቀፍ ደረጃ 3.4 ቢሊዮን ሕዝብ የሞባይል ኢንተርኔት ሽፋን ባላቸው አካባቢዎች እየኖሩ አገልግሎቱን እንደማይጠቀሙ ተመላክቷል። በተለይም ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት የመግቢያ ደረጃ የስማርትፎን ዋጋ ለአነስተኛ ገቢ ካላቸው ዜጎች ወርሃዊ ገቢ 76 በመቶውን እንደሚሸፍን የተገለጸ ሲሆን፣ የስልክ ዋጋን ለመቀነስ ከፋብሪካዎች እና ከመንግስታት ጋር መስራት እንደሚገባ ታምኖበታል። በተጨማሪም የሳይበር ማጭበርበሮችን መታገል እና የወደፊቱን የ 6G ቴክኖሎጂ ማዘጋጀት የዘርፉ ቅድሚያ ጉዳዮች ናቸው።
🔗 TechAfrica News
#GSMA #5G #Connectivity

TechAfrica News
GSMA Board Sets Global Priorities for 5G Investment, Digital Inclusion and 6G
With 5G adoption accelerating across markets, discussions focused on how sustainable market structures can support investment in new technologies and how advanced capabilities, including network slicing, can create value across the wider economy. By 2030…
October 13, 2026 41