Enza Capital ለአፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተዋይነት (AI) ስታርታፖች አዲስ ፈንድ ይፋ አደረገ
በአፍሪካ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ላለፉት ሰባት ዓመታት ኢንቨስት ሲያደርግ የቆየው የቬንቸር ካፒታል ተቋም Enza Capital ለአህጉሪቱ የሰው ሰራሽ አስተዋይነት (AI) እና ከAI ጋር የተያያዙ ስታርታፖች የሚሆን አዲስ ፈንድ ይፋ አደረገ። በድርጅቱ ማኔጂንግ ፓርትነር Mike Mompi የሚመራው ይህ ተቋም እስከ አሁን ባሰባሰባቸው የመጀመሪያዎቹ ሁለት ፈንዶች 58 ሚሊዮን USD ካፒታል ያንቀሳቀሰ ሲሆን፣ በ9 የአፍሪካ ሀገራት በሚገኙ 47 ኩባንያዎች ላይ 75 የኢንቨስትመንት ውሳኔዎችን አከናውኗል። Enza አዲሱን ፈንድ ያስጀመረው ልዩ ትኩረት ያላቸው ፈንዶች አዳዲስ ስታርታፖችን በብቃት ለመደገፍ ያስችላሉ በሚል እምነት ነው።
በ2025 ከዓለም አቀፍ የቬንቸር ካፒታል ኢንቨስትመንት 60 በመቶ ያህሉ ወደ AI ዘርፍ የተመራ ቢሆንም፣ የአፍሪካ ድርሻ ከ5 በመቶ አይበልጥም። Enza Capital ይህንን ክፍተት ለመሙላት ትላልቅ የዓለም አቀፍ ሞዴሎችን ከሚገነቡ ኩባንያዎች ጋር ከመፎካከር ይልቅ ከአፍሪካ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር የሚጣጣሙ የAI መፍትሔዎችን፣ የአካባቢ ቋንቋዎችን የሚረዱ የድምፅ ቴክኖሎጂዎችን፣ የተገደበ የኢንተርኔት ግንኙነት ባላቸው አካባቢዎች የሚሰሩ እና የሀገር ውስጥ መረጃዎችን የሚጠቀሙ ኩባንያዎችን ትኩረት አድርጎ ለመደገፍ አቅዷል።
🔗 TechCabal
#AI #Africa #VentureCapital

TechCabal
Why Enza Capital is betting on a fund just for AI
Enza Capital has launched a dedicated fund just for artificial intelligence (AI) startups and AI-enabled startups in Africa.
November 2, 2026 20