የሰበር ችሎቱ ውሳኔ የሰበር ሰሚ ችሎቱ የአመልካችን የጥፋተኝነት ውሳኔ ቢያጸናም፣ በካሳው መጠን ላይ… — Elias Kasa Legal Service. — TG.ME

የሰበር ችሎቱ ውሳኔ የሰበር ሰሚ ችሎቱ የአመልካችን የጥፋተኝነት ውሳኔ ቢያጸናም፣ በካሳው መጠን ላይ የተሰጠውን ውሳኔ ግን እንደሚከተለው አሻሽሎታል፡- የስም ማጥፋት ጥፋተኝነት መጽናቱ፦ የባንክ መልካም ስም የህልውናው መሠረት በመሆኑ፣ አመልካች ምክንያቱን ሳይገልጽ በጥቅሉ ከባንኩ ዋስትና አንቀበልም ብሎ መጻፉና ለሌሎች አካላት ማሰራጨቱ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2109 መሠረት መልካም ስምን የሚያጎድፍና ተጠያቂነትን የሚያስከትል ተግባር ነው። የካሳ መጠን መሻሻሉ፦ በደረሰው ትክክለኛ ጉዳት ላይ በቂ ማስረጃ በሌለበት ሁኔታ የጠየቀውን ሙሉ የካሳ መጠን መፍቀድ ተገቢ ስላልሆነ፣ ጉዳቱ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2102 መሠረት በርትዕ (Equity) ሊሰላ ይገባል። በዚህም መሠረት የካሳው መጠን ወደ 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ዝቅ እንዲል ተወስኗል። መሠረታዊ የሕግ ምክንያት (Ratio Decidendi) በባንክ መልካም ስም ላይ የሚፈጸም ሕገ-ወጥ ድርጊት፦ የፋይናንስ ተቋማት (ባንኮች) ለደንበኞቻቸው በሚሰጡት አገልግሎት ላይ ያላቸው መልካም ስም የህልውናቸው መሠረት ነው። በመሆኑም፣ ያለ በቂና ግልጽ ምክንያት ከአንድ የተወሰነ ባንክ የሚቀርብ የዋስትና ሰነድ ተቀባይነት እንደሌለው በጥቅሉ የሚገልጽ ደብዳቤ መጻፍና ለሌሎች አካላት ማሰራጨት፣ የባንኩን ታማኝነትና ብቃት ጥያቄ ውስጥ የሚጥል በመሆኑ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2109 መሠረት መልካም ስምን እንደማጥፋት ይቆጠራል። በመልካም ስም መጥፋት ወይም በሌላ ሕገ-ወጥ ተግባር ምክንያት የደረሰን ትክክለኛ የጉዳት መጠን በሒሳብ ወይም በማስረጃ ለይቶ ለማወቅ አስቸጋሪ በሆነበት ሁኔታ፣ ፍርድ ቤቶች ተጎጂው የጠየቀውን ሙሉ የካሳ መጠንመፍቀድ የለባቸውም። ይልቁንም፣ እንዲህ ዓይነቱ ካሳ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 2102 መሠረት በርትዕ ሊወሰንና ሊሰላ ይገባል፡፡

August 11, 2026 4.6K 24