ውድ የቻናላችን ተከታታዮች፤ ቀደም ሲል በሌሎች ሀገራት የሕግ ሥርዓትና በዓለም አቀፍ ደረጃ የዳኝነት ጀግንነት… — Elias Kasa Legal Service. — TG.ME

📌 ውድ የቻናላችን ተከታታዮች፤ ቀደም ሲል በሌሎች ሀገራት የሕግ ሥርዓትና በዓለም አቀፍ ደረጃ የዳኝነት ጀግንነት (Judicial Courage) ያለበትን ደረጃ፣ መገለጫዎችና የታዩ ታሪካዊ የፍርድ ውሳኔዎችን የሚዳስሰውን አጠር ያለ ጽሑፍ ማካፈላችን ይታወሳል። አሁን ደግሞ፣ ያንን መሠረታዊ ዓለም አቀፋዊ እሳቤ ወደ እኛ ሀገር ተግባራዊ እውነታ በማምጣት፣ ጉዳዩን በኢትዮጵያ የሕግ ሥርዓት መነጽር በጥልቀት የሚመረምረውንና “በኢትዮጵያ የሕግ ሥርዓት ውስጥ የዳኝነት ጀግንነት፡ በጎ ምግባር፣ ግዴታ እና የሕገ-መንግሥታዊ ፍትሕ አስፈላጊነቶች” (Judicial Courage in the Ethiopian Legal System: Virtue, Duty, and the Imperatives of Constitutional Justice) በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን አጭር ምልከታ ይዘንላችሁ ቀርበናል። ይህ አጭር ጽሑፍ፦ - በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥታዊና የሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ለዳኝነት ነጻነት የተሰጡትን መደበኛ ዋስትናዎች፤ - በተግባር ያሉትን የፖለቲካ ጣልቃገብነቶች፣ መዋቅራዊ ድክመቶችና የታሪክ ፈተናዎች፤ - የዳኝነት ጀግንነት በጉልህ የታየባቸውን የፍርድ ቤት ውሳኔዎች (በተለይም በግል ሕግና በንግድ ክርክሮች) እና በሌላ በኩል ደግሞ በፖለቲካዊና በሰብአዊ መብት ጉዳዮች ላይ የታዩትን ክፍተቶች፤ እንዲሁም - የሕግ የበላይነትን እውን ለማድረግ ወደፊት ሊወሰዱ የሚገባቸውን የማሻሻያ አቅጣጫዎች በአጭር ባጭሩ ያስቀምጣል። ከቀደመው ዓለም አቀፋዊ ዳሰሳችን ቀጥሎ፣ የዚህ በኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ምልከታ ከዚህ መልእክት በላይ ተያይዞ (Attached) የቀረበ በመሆኑ ሰነዱን በመክፈት እንድታነቡት እንጋብዛለን። 📖 መልካም ንባብ! ጽሑፉን ካነበባችሁ በኋላ ያላችሁን ሙያዊ አስተያየት አስቀምጡ!

August 11, 2026 2.9K 9