Elias Kasa Legal Service.: post #7828 — TG.ME

የባለስልጣናት እና የዳኞች የአገልግሎት ዘመን ስሌት እና የጥቅማጥቅሞች፡-የፌዴሬሽን ም/ቤት ትርጉም ምልከታ ውድ የቻናላችን ተከታታዮች፤ ከአገልግሎት ለሚሰናበቱ የመንግስት እና የሀገር መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የፓርላማ አባላት እና ለዳኞች የሚደረገው የአገልግሎት ዘመን ስሌት እና የጥቅማጥቅም አመዳደብ የተቋማዊ ነፃነትን፣ የጡረታ ተንቀሳቃሽነትን (Portability) እና የሕግ የበላይነትን ለማስጠበቅ የሚያስችል እጅግ ወሳኝ የሕዝብ ሕግ (Public Law) ማዕቀፍ ነው። ይህ አጭር ጽሑፍ የዳበረ የዲሞክራሲና የዳኝነት ስርዓት አላቸው ተብለው የሚታወቁትን የጥቂት አገራት የሕግ ማዕቀፎችን ከማነፃፀሩ ባሻገር፤ የኢትዮጵያ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በፋይል ቁጥር 154 የቀረበለትን ጉዳይ መነሻ በማድረግ በአዋጅ ቁጥር 653/2001 አንቀጽ 53(3) ትርጓሜ ላይ የሰጠውን ህገ መንግስታዊ ትርጉም እና ቀድሞ በክልል የተሰጠ አገልግሎት ለፌደራል ዳኞች የጡረታ ስሌት የሚኖረውን ህገ-መንግስታዊ እና መዋቅራዊ ፋይዳ በስፋት ይተነትናል። 📄 ምንም እንኳን ፅሁፉ የምርምር ስነ ዘዴዎችን በጥብቅ በመከተል የተፃፈ ባይሆንም(ወደፊት በጥልቀትና አካዳሚያዊ ደንቦች አግባብ የሚዳብር መሆኑ እንደተጠበቀ ሁኖ) ለውይይት መነሻ ይሆናል በሚል እምነት የጽሑፉን ሙሉ ይዘት (Full Article) እና የም/ቤቱን ውሳኔ(በድጋሚ) ከላይ እንዲያያዝ የተደረገ በመሆኑ ሰነዱን በመክፈት ማንበብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። መልካም ንባብ! አልማው ወ.

❤1👍1
August 11, 2026 2.6K 5