በማለት ኢብን ተ'ይሚያን ነፃ ለማድረግ ሐዲሱን በደንብ ባለመረዳት እመት ዐኢሻህን ረዲየሏሁ ዓንሃ በፈጣሪዋ ላይ ባላት እምነት ጎዶሎ ማድረግ ውጤቱ ሆኗል። ለዚህም በቅርቡ በአዲስ ዝግጅት እመለስበታለው።
ሌላው በተእዊል ከሆነ ብሎ ኢብን ተ'ይሚያን ላለማክፈር ያነሳቸው ደዋቢጦች ኢብን ተ'ይሚያህ ሚያህል ሓፊዝ በየትኛውም በተጠቀሱ የስድ ደዋቢጦች ዓቂል፣ባሊግ ሆኖ ያለ ምላስ ወለምታ እስከተናገረው ድረስ ተእዊል የሚለው በዚህ ቀጥዕይ ጉዳይ ላይ ላለመክፈር ዑዝር ሊያሰጠው የሚችል ምንም ነገር ፈፅሞን አይኖርም።ለዚህም ረምልይ ባዘጋጁዋት በሚንሃጅ ሸርሓቸው ላይ አሕመድ ብኑ ዓብዲረዛቅ አል-መግሪቢይ አ'ረሺድይ በመባል ሚታቁት 1096 አመተ ሂጅራ የሞቱት እንዲህ ሲሉ የተእዊል ጉዳይ በስድ ለሁሉ ነጥብ ድርሻን ይዞ እንደ ዓቂል መሆን የሚጠየቅበት እንዳልሆነ በዚህ መልኩ ያስረዳሉ፦
قَالَ الْمُحَشِّي عَلَى الرَّمْلِيِّ أَحْمَدُ بنُ عَبْدِ الرَّزَّاقِ الْمَعْرُوفُ بِالْمَغْرِبِيِّ الرَّشِيدِيِّ الْمُتَوَفَّى سَنَةَ أَلْفٍ وَسِتٍّ وَتِسْعِينَ «قَوْلُهُ «وَاجْتِهَادٍ» أَيْ فِيمَا لَمْ يَقُمِ الدَّلِيلُ الْقَاطِعُ عَلَى خِلافِهِ بِدَلِيلِ كُفْرِ نَحْوِ الْقَائِلِينَ بِقِدَمِ الْعَالَمِ مَعَ أَنَّهُ بِالِاجْتِهَادِ» اهـ
[“(ኢጅቲሃድ አልያ በተእዊል) ማለታቸው ከእርሱ በተቃራኒ ማስረጃ ባልቆመበት ላይ ነው።ለዚህም ዐለምን ጅምር የላትም በማለት የከፈሩ ሰዎችን የመሰለ: ይህም ከነርሱ በኢጅቲሃድ (ተእዊል) ከመሆኑም ጋር ነው”]
በማለት ተእዊል ማድረግ ሁሌ ኩፍር ላይ ከመውደቅ እንደማይከለክልና በነዚህ ባሉ ቦታዎች ደግሞ ፈፅሞን እንደ ቅድመ ሁኔታ እንደማይታይ ያስቀምጣሉ።ዓለምን ጅምር የላትም ያሉ ሰዎች በተእዊል ቢሆንም ነገር ግን ተእዊል ሁሌ ተክፊርን አይከለክልምና፤ ይህን ያለ ሰው ይከፍራል ሲሉ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ማለት ይህ ነው። አንደኛው ተእዊል ሁሉ ቦታ ኩፍር እንደማይከለክልና። ሁለተኛ ኢብን ተ'ይሚያህ በዚህ ንግግሩ ካፊር እንደሆነ እየገለፁ ነው።ኢብን ተ'ይሚያህ በዚህ ዓለምን ጅማሬ የላትም ባለበት ንግግሩ የቁርኣንና የሓዲስን ህግጋቶች ከመተላለፉ አልፎ በዚህም አቋሙ ላይ እርሱን የማክፈር ብያኔ ከምስራቅ እስከ ምዕራቡ ዳርቻ ያሉት ምእመናን እንደሰጡ በጥቂቱ እንገልፃለን ከነርሱ መሀከልም፦
وقال الحافظ اللغوي محمد مرتضى الزبيدي في شرح الإحياء عند الكلام على تكفير الفلاسفة ما نصه (21) "ومن ذلك قولهم بقدم العالم وأزليته، فلم يذهب أحد من المسلمين إلى شىء من ذلك" اهـ،
① አል-ሓፊዙ አ'ሉገውዩ ሙሐመድ ሙርተዶ ኣ'ዘቢድይ "ኢትሓፉ ሳዳቲል ሙተቂይን"ብለው በሰየሙት ኪታብ ላይ ስለ ፋላስፋዎች መክፈር ሲጠቅሱ ይህን ይላሉ፦[“ከንግግራቸው መሀከል ዓለም ጅምር የላትም የሚለው ይገኝበታል። አንድም ሙስሊም እነርሱ ባሉበት የተጓዘ የለም”]። ይህ ከሳቸው የተሰጠ የተክፊር ፍርድ እንደሆነ ልብ ሊባል ይገባል። ምክነያቱም በዚህ መንገድ የተጓዘ እንደሆነ ሙስሊም የለም፤ ሲሉ በዛ መንገድ የተጓዘ ኢማኑ የተነጠቀ እንደሚሆን አስምረውበታል።
وقال الحافظ ابن حجر العسقلاني في فتح الباري (20) ما نصه "قال شيخنا- يعني العراقي- في شرح الترمذي: الصحيح في تكفير منكر الإجماع تقييده بإنكار ما يعلم وجوبه من الدين بالضرورة كالصلوات الخمس، ومنهم من عبر بإنكار ما علم وجوبه بالتواتر، ومنه القول بحدوث العالم، وقد حكى القاضي عياض وغيره الإجماع على تكفير من يقول بقدم العالم،
② አል-ሓፊዙ ኢብኑ ሓጀር አል-ዓስቀላንይ "ፈትሑል ባሪይ" በተሰኘው የሶሒሑል ቡኽርይ ሸርሓቸው ላይ ይህን ሲሉ ያስቀምጣሉ፦[“ሸይኻችን (ኣል-ዒራቅይ ማለታቸው ነው)በሸርሑ ኣ'ቲርሚዝይ ላይ"ኢጅማዕን የጣሰ ይከፍራል" የሚለው ንግግር ትክክሉ "ኢጅማዕ የተደረሰበት ነጥብ ግዴታነቱ ሁሉ ዘንዳ የተሰራጨ በሆነ ጉዳይ መሆን አለበት" ተብሎ መለየት ያስፈልገዋል። ለምሳሌ እንደ አምስት ግዜያት ሶለዋቶችን ያለ ይመስል።ከነኚህ ዑለማዎችም መሀከል ስለዚህ ገለፃ ሲያደርግ "ግዴታነቱ በተዋቱር የመጣን ነገር መቃወም በማለት ያስቀምጣሉ"። ከዚህ ጉዳይ መሀከልም የዓለም ጅማሬ መኖር ይገኝበታል።አልቃዲይ ዒያድ እንዲሁ ሌሎችም “ዓለምን ጅማሬ የላትም ብሎ በተናገረ ላይ #ካፊር እንደሆነ የጋራ አቋም አስቀምጠዋል”]።
وقال في موضعءاخر منه ما نصه (22) "وقال السبكي في شرح عقيدة ابن الحاجب: اعلم أن حكم الجواهر والأعراض كلها الحدوث،ا فإذًا العالم كله حادث، وعلى هذا إجماع المسلمين بل وكل الملل، ومن خالف في ذلك فهو كافر لمخالفة الإجماع القطعي" ا.هـ.ا
በሌላ ቦታ ላይ በዛው ፈትሑል ባሪይ ኪታባቸው ኣ'ሱብክይ "ሸርሑ ኢብኒል ሓጂብ" ላይ እንዲህ ብለዋል ይላሉ፦[“የመጠን እንዲሁ የመጠን ባህሪያቶች ሁሏም ፍጥረት ናቸው።ስለዚህም ዓለም በጠቅላላው ፍጡር ነው። በዚህም ላይ የሙስሊሞች የጋራ አቋም #ታስሯል። ይልቅንስ ከእስልምና ውጪም ያሉ እምነቶች በዚህ ላይ ያፀናሉ። በዚህ ላይ የተቃረነ #ካፊር ነው። ምክነያቱም በቁርጥ የታወቀን የሆነ የኢጅማዕ አቋም ተላልፏልና”]።
قال القاضي عياض في الشفا (19) "وكذلك نقطع على كفر من قال بقدم العالـم أو بقائه أو شك في ذلك على مذهب بعض الفلاسفة والدهرية" اهـ.ا
③ አል-ቃዲይ ዒያድ "ኣ'ሺፋ" በተሰኘው ኪታባቸው ላይ እንዲህ ይላሉ፦[“እንዲሁ እንደ ከፊል ፈላስፋዎች እንዲሁ ደህሪያዎች ዓለምን ጅማሬ የላትም አልያ ዘውታሪ ናት፤ብሎ በተናገረ አልያ በተጠራጠረ ሰው በኩፍሩ ላይ በቁርጥ #እንወስናለን”]።
نقل المحدّث الأصولي بدر الدين الزركشي في تشنيف المسامع (18) اتفاق المسلمين على كفر من يقول بأزلية نوع العالم فقال بعد أن ذكر أن الفلاسفة قالوا: إن العالم قديم بمادته وصورته، وبعضهم قال: قديم المادة محدث الصورة، ما نصه "وضلَّلهم المسلمون في ذلك وكفروهم" اهـ.
④ አል-ሙሐዲሱ አል-ኡሱልዩ በድሩ ዲን አ‘ዘርከሽይ የዐለምን መሰረት ጅማሬ የለውም ያሉትን ፈላስፋዎች ንግግራቸውን በ "ተሽኒፉል መሳሚዕ" ብለው በሰየሙት ኪታብ ከጠቀሱ ቡሀሏ በዚህም በመክፈራቸው ላይ የዑለማእን የጋራ አቋም ሲያስተላልፉ እንዲህ ይላሉ፦[“በእርግጥም ሙስሊሞች በዚህ ላይ አጥምመዋቸዋል ብሎም አክፍረዋቸዋል”]።
ከዚህ ሁሉ የዑለማእ የጋራ አቋም ቡሀሏ የተለመደው ኺላፍ አለበት ምትለው ማታለያቹህ የምትሰራ አትሆንም።አልያ አሏህን ፈጣሪ አይደለም ያለ ሙስሊም ነው ትላላችሁ አልያ ካፊር ነው በማለት ኢብን ተ'ይሚያን በመተው የዑለማኡል ኣዕላምን መንገድ ትይዛላችሁ።
13May 5, 2026 2.2K 6