መረጃ ይዳኘን ❿
قال الله تعالى"يُضِلُّ بِهِ كَثِيرًا وَيَهْدِي بِهِ كَثِيرًا ۚ وَمَا يُضِلُّ بِهِ إِلَّا الْفَاسِقِينَ" سورةُ البقرة ٢٦
[“ በርሱ (በምሳሌው) ብዙዎችን ያጠማል።በርሱም ብዙዎችን ያቀናል፡፡በርሱም አመፀኞችን እንጅ ሌላን አያጠምም”] "ሱረቱል በቀራህ 26"
ፍትሓዊው ጌታ አሏህ ሁሉ የእርሱ ንብረት ነው። በችሮታው ያሻውን ገነት ቢያስገባ ቀሪውን በፍትሑ ቢቀጣ ውዳሴ እንዲሁ ልቅና እንጂ ፈፅሞን ውሳኔው ላይ ውግዘት አይታሰብም።ሁሉ የእርሱ ሁሉም ወደርሱ፣ ሁሉ ለእርሱ ተገዢ: ጉዳዩም ሁሉ ወደ እርሱ ተመላሽ ነውና።
መሃሪው ጌታ አሏህ ነብያትን ያወጣበት ሰው የተባለን ዘር ከሁሉ ዘሮች በጥቅሉ አብልጦታል። ብሎም ይህ ዘር ከእርሱ ውስጥ ለፈጠረው ሀያል ጌታ ተገዢ እና ተዋዳቂ በትዕዛዙ በነብያቱ በኪታቡም ተመሪ ቢኖርም፤በተቃራኒው ደግሞ ሊመራበት ዘንዳ በተሰጠው መፅሀፍ አስተባባይ ሊመራው ሰበብ በመሆን በተላከለት ነብይ ክዶና አምፆ እሚገኝ ዘመን የተረከለን እልፈ አላፍ ለቁጥር ሚያዳግት ሆኖ ይገኛል።
ነብዩና ሙሐመድ ﷺ በብዙ ትውፊቶቻቸው እንዲሁ ለእርሳቸው በተላከው ቁርኣን ላይ ጥቂት በማይባሉ አናቅፅቶች ውስጥ የአሏህን ፈጣሪነት የሌሎችን ፍጡርነት የአሏህን ጅማሬ አለመኖር የሌሎችን ግኝነት በዝርዝር አስፍረውና እንዲሁ ሰፍሮ ምናገኘው ከኢማን መሰረታዊ ነጥብ ከሆኑት ውስጥ የሚመደብ ችላ ማይሰኝ ትልቅ ጉዳይ ነው።
አሏሁ ጀለ ጀላሉሁ በሱረቱል ኣ'ዙመር አንቀፅ 62 ላይ እንዲህም ይላል፦
قالَ اللهُ تعالى" اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ" الزمر آية 62
[“አሏህ የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው”]
አንድ ግለሰብ ይህን ሶሪሕ የሆነ አንቀፅ እተርጉማለው በማለት የያዘውን ፍቺ ማጣመም አይበቃለትም።በዚህም አንቀፅ አሏህ የራሱን ፈጣሪነት የሌሎችን ደግሞ ፍጡርነት አፅድቋል። ይህም ሲፈታ አሏህ ጅማሬ የለውም ሌላው ደግሞ ጅምር አለው የተገኘ ነው ሚለውን ያለ ምንም ጥርጥር የሚያስረዳ ነው።
የአሏህን ኪታብም ከሁሉ በላይ ተገንዛቢ የሆኑት ትልቁ ሰው ነብዩ ሙሐመድﷺ"አልቡኻርይ" በዘገቡት ሓዲሳቸው ከየመን በሕቡእ ሆነው በመምጣት ስለ መጀመርያው ፍጡር ምንነት ለጠየቋቸው ሰዎች እንዲህ ሲሉ መልሰዋል፦
قالَ عليه الصَّلاةُ السَّلامُ "كانَ اللهُ ولَم يَكُنْ شَيءٌ غَيرُه" رواهُ البخاريُّ
[“አሏህ ነበር ምንም ነገር ከመኖሩ በፊት”]።
ይህ ሓዲስ ብዙ ቁም ነገሮችን ይዟል።ነገር ግን የማስረጃ ቦታውን በመጥቀስ ሲታጠር ነብዩ ﷺ ለነኚህ ሰዎች በመጀመርያ የአሏህን ጅማሬ አለመኖር አፅድቀውላቸዋል።ምክነያቱም ከእውቀቶች ሁሉ ሊቀደም የሚገባው አሏህን ማወቅ እንደሆነ እኚህ ትልቁ ሰው በመንገዳቸው ምልክት እየሰጡን ነው።ቀጥሎም ከእርሱ ውጪ ያለ በጠቅላላ ከእርሱ ጋር እንዳልነበርና አሏህ እንደፈጠረው ገለፃ አድርገዋል።ሐዲሱም ይቀጥላል…
ብሎም አንድ ሰው ነብዩﷺያሉት ከእርሱ ውጪ ምንም አልነበረም ቢሆንም ነገር ግን "ምንም" የሚለው ቃል በራሱ ጥቅላዊ ውጤት እንዴት ያሲዛል ካለ እኛም በምላሹ ዑለማዎች ዘንዳም ምትታወቅ አንድ መመርያ አለች እርሷም "ነኪራህ የሆነች ቃል በነፍይ የንግግር ዘይቤ ላይ ከመጣች ጥቅላዊ ትርጉምን ትሰጣለች" ይህም ማለት ነብዩﷺሓዲሳቸው ላይ "شيء" የሚልን ቃል ተጠቅመዋል ይህች "ነኪራህ" ትሰኛለች። "ነፍይ" ደግሞ "لَمْ" የምትሰኘዋ ናት። ሁለቱ በአንድ ዐ.ነገር ሲጣመሩ ትርጉማቸው ጥቅልን የሚያሲዝ በዚህ ሓዲስ ደግሞ ከአሏህ ውጪ ያለን የሁሉንም ጅማሬ አለመኖር የሚያስክድ፤ፍጥሩነቱን ደግሞ የሚያፀና ነው።በዚህም ጅማሬ አለመኖርን ለአሏህ ብቻ የሚያረጋግጥ ይሆናል በማለት ገለፃ እናደርግለታለን”]።
በዚህ ርዕስ በዒልማቸው ከጠመሙ ሰዎች መሀከል ኢብን ተ'ይሚያህ አል-ሓራንይ አንዱ ሲሆን በዚህም የፈላስፋዎችን መንገድ በመከተል ዓለም ጅምር የላትም(አሏህ አልፈጠረውም) በማለት "መጅሙዑ'ል ፈተዋ" በተሰኘው ኪታቡ ላይ ሙጀለድ 10 ገፅ 142 ላይ እንዲህ ሲል ያሰፍራል፦
ففي كتابه المسمى مجموع الفتاوى، المجلد العاشر، صحيفة 142، يقول ابن تيمية(وإن قدر أن نوعها لم يزل مع الله فهذه المعية لم ينفها شرع ولا عقل) وهذا من أشنع الكفر.
[“የዓለም መሰረቱ ጅማሬ የለውም የሚለው ታሳቢ ተደርጎ ከሆነ "የዓለምን መሰረት ጅማሬ አለመኖር ሸሪዓም ሆነ አዕምሮ አይክደውም”]።
በማለት ሽምጥጥ አድርጎ እረ ሸሪዓ እራሱ የዓለምን ጅማሬ አለመኖር አይክድም፤ አዕምሮ ሊክደው ይቅርና!? በማለት እጅ በአፍ በሉት እጅ በእግር የሚያሲዝ ዓቂል ሊያምንበት ቀርቶ እብድ ሊናገረው ሚከብድ ሃሳብ ሲያንተርስ ይታያል። ይህን የመሳሰሉ ጥመቶቹን በይፋ ለተመለከተ ዘይኑዲን አል-ዒራቅይ ስለ ኢብን ተ'ይሚያህ "ኣል-አጅዊበቱል-መርዲያህ" ብለው በሰየሙት ኪታብ ላይ እንዲህ በማለት መሳለቃቸው እውን ነው ያስብላል፦
عِلْمُهُ أكبرُ من عقلِهِ
[“እውቀቱ ከጭንቅላቱ የበለጠ ነው”]
ውዳሴ መስሎህ እንዳትሞኝ ይልቅንስ ጆሮ ሚያሲዝ ውግዘት እንጂ።የሆነው ሆኖ ነብይ የተላከለትና ተኣምራትን ከሙሳ ዓለይሂ ሰላም የተመለከተም ፊርዓውን ፈጣሪ ነኝ ከማለት አልተመለሰምና፤ ነገርዪው በእውቀት ብቻ ምንከላከለው ሳይሆን ቁልፉ ያማረ አሟሟት መሆኑን መዘንጋት የፊርዓውንና የኢብን ተ'ይሚያህን መጨረሻ ላየ ሚደበቅ አይሆንም።ለዛም ነው የገትይ ደረሳ የሆኑት አ'ሸይኽ ጀውሃር ብኑ ሓይደር፦
يَا ربّنَا بِحُسنِ الختامِ
[“ጌታችን ሆይ መልካም አሟሟትን”] በማለት ቀን ከሌት ሲማፀኑ የመዋላቸው ሚስጥር፤ በመሆኑም ከቅርብ ግዜ ወዲህ ለኢብን ተ'ይሚያህ የተለያዩ ማዕረጎችን በመለጠፍ ለዚህ ግልፅ ለሆነው የኩ*ፍ*ር ንግግሩ ለመከላከል ሲጋጋጥ ያገኘሁት #አደም ሙሐመድ ይህን ንግግር ባልሰማ ጆሮ ዳባ በማለት ኢብን ተ'ይሚያህን ሸይኽል ኢስላም ብሎ እስከመሰየም የመዳፈሩን ጉዳይ ስንመለከት ይህ ከናዳ ማውረድ ዑለማእን ኮርስ የመስጠት የዳና መውረድ አጀንዳ በነርሱ ላይ የተያዘ ስላቅ እንጂ ለፍሬ የታጨ ጉዳይ አለመሆኑ ልብ ያስብለናል።
በነገራችን ላይ ከኮርሱ ስላቅ በፊት በብዙ ጉዳዮች ላይ ከጅምሩ የውድቀትን መንገድ እያስተናገደ የመጣው አደም ሙሐመድ በቅርቡ "ዶዋቢጡ ተክፊር" ብላ በተሰየመችው ሪሳላህ ስለ መክፈርያ ነጥቦቹ ሲዘረዝር ለሰማው ጉድ ለካ ጅህልናም እንዲህ ይሰፍራልን በማለት ማስተዛዘቡ አይቀሪ ነው። እንዲሁ አንዱ ከሌላው ሚጣረስና ከተሕቂቅ በፀዱ ንግግሮች መመርኮዙን ላስተዋለ የዒልም ሰው ሳይሆን የህልም ሰው መሆኑን ያውጃል።
በመሆኑም የዓለምን ጅማሬ አለመኖር የሚያምነው ኢብን ተ'ይሚያህ ከራሱ አልፎ እነ ተቂዩዲን ኣ'ሱብክይም ይህን ንግግሩን በምስክርነት አኑረውታል።ይህንንም መካድ የነኚህን ታላላቅ ዑለማእ አመኔታ ማራቆት ተደርጎ ያስወነጅላል። ኢብን ተ'ይሚያን በዚህ ንግግሩ ላለማክፈር ዑዝር ለመፈለግ አደም ሙሐመድ ያነሳቸውን ማስረጃ ለተመለከተ በግዜ አቁሙሉን የሚል ጠያቂም ከተመልካች አይጠፋም። ከዛ ውስጥ አንዱ የእናታችን ዓኢሻህን (አሏህ በሰዎች የውስጥ ሚስጥር) ምንም ነገር ከእርሱ እንደማይደበቅበት አታውቅም ነበር በማለት ነብዩም "አሏህ ያውቃልን" በሚለው በዚህ ጥያቄዋ "አዎ ያውቃል" የሚል መልስ እንጂ አላከፈሯትምና: አንዳንድ በጅህልና ዑዝር ሚሰጡባቸው ባህሪዎች አሉ
9May 5, 2026 1.4K 6