የጡረተኞችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል .....///..... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ… — EEP Communication — TG.ME

የጡረተኞችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል
.....///.....
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቀድሞ ሠራተኞች የተመሠረተው ‎የመብራት ኃይል ሠራተኞች ጡረተኞች ማህበር ሦስተኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

የጉባዔው ሰብሳቢ ወ/ሮ ናዝሬት ዘለቀ እንደገለጹት የማህበሩ አባላት በእድሜ ገደብ ምክንያት ከተቋማቱ በጡረታ ቢገለሉም እንደሀገር በኃይል ልማት ዘርፍ ለተመዘገበው ውጤት የድርሻቸውን ተወጥተዋል።

የአባላቱን ግንኙነት በማጠናከር የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመቅረፍና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ማህበሩ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

የተሻሻለው የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብን ጨምሮ የሥራ አሥፈጻሚና የፋይናንስ ሪፖርት በማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ተሾመ መርዕድ እና በማህበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ መኮንን ክፍሌ ቀርቦ በጉባዔተኛው ጸድቋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚን በመወከል መልዕክት ያስተላለፉት የኮርፖሬት ፋይናንስና ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደመረ አሰፋ እንደገለጹት ለረጅም ዘመናት ያገላገላችሁበትን ተቋም የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርስ እና አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር መልካም ጅምሮችን በማጠናከርና አዳዲስ ዕይታዎችን በመጨመር እየተሰራ ነው።

በተደጋጋሚ ከጡረተኞች የሚነሱትን የህክምና ጨምሮ ሌሎች ጥያቄዎችን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በመሆን ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ አብራርተዋል።

የኢትየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚን በመወከል መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ኢሳያስ ደንድር በበኩላቸው ጡረተኞች የኃይል ዘርፉ አሁን የደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ በጎ አሻራቸውን ያሳረፉ የሀገር ባለውለታ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

የተቋማቱን አሰራርና ሕግ በተከተለ መልኩ ከማህበሩ ጋር በቅርበትና በትብብር በመስራት የጡረተኞችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ሥራዎች መኖራቸውንም አስታውሰዋል፡፡

በጡረተኞች የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት የሁለቱ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ተቋማቱን ለማሳደግና ለማዘመን በሚደረገው ጥረትም ጡረተኞች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et
ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም
❤4
August 29, 2026 3.1K 2