ማከፋፈያ ጣቢያው የሀገሪቱን የኃይል ሲስተም በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው… — EEP Communication — TG.ME

ማከፋፈያ ጣቢያው የሀገሪቱን የኃይል ሲስተም በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያበረከተ ነው
……..///…….
የሆለታ ባለ 500 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመነጨውን ኃይል ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት በማስገባት እና ቮልቴጅን በማረጋጋት ቁልፍ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ የጣቢያው ኃላፊ ገለጹ።

ኃላፊዉ አቶ ጥላሁን አዘዘው እንደገለፁት በ2008 ዓ.ም. ሥራ የጀመረው ማከፋፈያ ጣቢያው ኃይል በመሸከም እና በቴክኖሎጂ አቅም ከፍተኛነት ከሚጠቀሱት መካከል አንዱ ነው።

ጣቢያው በሲስተሙ ውስጥ የቮልቴጅ መዋዠቅ እንዳይኖር አውቶማቲክ በሆነ መንገድ ቮልቴጁን የመቆጣጠር እና የመጠበቅ ስራ እንደሚሰራ ኃላፊዉ አብራርተዋል።

ጣቢያው ከህዳሴ በደዴሳ በኩል የሚመጣውን ኃይል ተቀብሎ ወደ 400 ኪሎ ቮልት በመቀነስ ለገላን፣ ለሰበታ እና ለሱልልታ ማከፋፈያ ጣቢያዎች የሚያደርስ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ.…
https://www.eep.com.et/?amh-news=ማከፋፈያ-ጣቢያው-የሀገሪቱን-የኃይል-ሲስ&lang=am

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric
📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication
📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power
📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia
📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et
ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም
❤11
August 31, 2026 2.4K 1 2