ሩፋኤል እላለው ሩፋኤል እላለው ድምጼን ከፍ አድርጌ የችግሬ ደራሽ ክብሬ ነው ማዕረጌ በፈዋሽ እጆቹ ድኖ ሳር… — ማኅበረ ኤዶምያስ ጠቅላላ መንፈሳዊ ማኅበር — TG.ME

ሩፋኤል እላለው

ሩፋኤል እላለው ድምጼን ከፍ አድርጌ
የችግሬ ደራሽ ክብሬ ነው ማዕረጌ
በፈዋሽ እጆቹ ድኖ ሳር ቅጠሉ
ሩፋኤል ይላል ፍጥረት በሙሉ

እስኪ ላመስግነው ከበሮዬን ላንሳ
ደዌና ሀዘኔ ሞቴ ከተረሳ
እንደ ዳዊት እጆች እጆቼን ላበርታ
ለምን ዝም እላለሁ ጩኸቴ ተሰምቷል
አዝ

የሚፊገመገመው ጉልበቴ በርትቷል
ሩፋኤል ደርሶልኝ ጨለማዬ በርቷል
እንባና ፀሎቴ በእጆቹ አረገ
ልቤን አስደመመው ድንቅ እያደረገ
አዝ

በሀይማኖት ያሉ በምነት የታዘዙ
ከወጥመዱ ተርፈው በሰላም ተጓዙ
ወደ ቤቱ ግቡ በታላቅ ምስጋና
የጦቢት አይኖች ፈውሶታልና
አዝ

የከበረ ሆኗል እጅግ የተፈራ
ፈታሔ ማህፀን ተዓምር የሚሰራ
አንካሳው ዘለለ ምርኩዙን ጣለና
ሩፋኤል ሲነሳ የጎበጠው ቀና

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
   •➢ ሼር // SHARE
👇👇👇

@edomiyass21
@edomiyass21
@edomiyass21
♡ሩፋኤል እላለው♡
❤1
September 7, 2026 110 11