እጀምራለሁ አዲሱን ቀን በምስጋና
ቸርነትህ ለዚህ አድርሶኛልና
ምህረትህ ዘመኔን ያድስ ጌታ ክርስቶስ
ምህረትህ ዘመኔን ያድስ አምላክ ክርስቶስ
ትናንትን አለፍኩት ቸርከኝ ይህን ዓመት
ተባርኳል ሕይወቴ አንተ ኖረህበት
ቃሉ የሚጠግን ሐዘን እየሻረ
ማን አለ እንደ አንተ(፪)እኔን ያከበረ
/ሁሌ አዲስ ነው የአንተ ፍቅር
ክበር እላለሁ ክበር/(፪)
አዝ= = = = =
አይተህ ቸል ያላልከኝ ጩኸቴን ሰምተህ
ቁስሌን የፈወስከው ሐኪሜ አንተ ነህ
በሚደነቅ ምህረት በደሌን የማርከው
ሥራኝ በዚህ ዓመት(፪)አድርገኝ አዲስ ሰው
/ሁሌ አዲስ ነው የአንተ ፍቅር
ክበር እላለሁ ክበር/(፪)
አዝ= = = = =
አእዋፍ በማለዳ ምስጋና ያቀርባሉ
ለሊቱ እንዳለፈ ብርሃን ያበስራሉ
ወራት እና ዓመታት ታድሰው ይመጣሉ
ኃያሉ እግዚአብሔር (፪)ክብርን ይገልጣሉ
እጹብ እጹብ የአንተ ሥራ
እንዲህ በቀላል አይወራ
ግሩም ግሩም የአንተ ሥራ
እንዲህ በቀላል አይወራ
አዝ= = = = =
አላማዬ አንተ ነህ ሕይወቴን የምትመራ
ማንነቴ ይመስክር ማዳንህን ያውራ
ይህን አመት ደግሞ ለንስሐ ተውከኝ
ፍቅር ነህ ጌታዬ(፪)እንዲሁ የወደድከኝ
እጹብ እጹብ የአንተ ሥራ
እንዲህ በቀላል አይወራ
ግሩም ግሩም የአንተ ሥራ
እንዲህ በቀላል አይወራ
መዝሙር
ዲያቆን ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ)
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
•➢ ሼር // SHARE
👇👇👇
@edomiyass21
@edomiyass21
@edomiyass21
