ዓለም አቀፍ የቡና ሁኔታን በወፍ በረር!!
የገበያ ሁኔታ
የአሜሪካ የግብርና ሚኒስቴር (USDA) በ2026/27 የምርት ዘመን የዓለም ቡና ምርት አዲስ እና ታሪካዊ ደረጃ ላይ ይደርሳል ሲል መግለጹ ተሰምቷል።
የዓለም የቡና ምርት በ10.8 ሚሊዮን ጆንያዎች በማደግ በድምሩ 189.7 ሚሊዮን ጆንያ በመድረስ አዲስ የምርት ጣሪያ ይመዘግባል ተብሎ ይጠበቃል። የዓለም አቀፍ የቡና ፍጆታ 179.7 ሚሊዮን ጆንያ ይደርሳል ተብሎ የተገመተ ሲሆን፣ የዓመቱ መጨረሻ የተጠራቀመ ክምችት ደግሞ ወደ 26.3 ሚሊዮን ጆንያ ያድጋል። ለዚህ የምርት እድገት ኢትዮጵያ፣ ብራዚል፣ ቬትናም እና ኡጋንዳ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ሲሆን፣ በተቃራኒው የኢንዶኔዢያ ምርት ከመጠን በላይ በጣለው ዝናብ ምክንያት በ1 ሚሊዮን ጆንያ ይቀንሳል ተብሏል።
በሳህለማርያም ገ/መድህን

August 21, 2026 2.6K 8