Ethiopian Coffee and Tea Authority: post #7384 — TG.ME

ሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ በሙዳ–ድኖቆሰ ቀበሌ በአርሶ አደር ጓሮ እየለማ የሚገኘው የቡና ልማት በአሁኑ ወቅት አበረታች ገጽታ እያሳየ ይገኛል።

በተለይም በቡና ዛፎቹ ላይ በብዛት የተያዙ የቡና ፍሬዎች የልማቱን የምርት አቅም የሚያሳይ ሲሆን፣ በጓሮ ልማት ውስጥ ከበቆሎና ሌሎች ሰብሎች ጋር ተቀናጅቶ መልማቱም የመሬት ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያግዝ ነው።

የጓሮ ቡና ልማት ለአርሶ አደሩ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ከመፍጠሩም በላይ የቤተሰብ ኢኮኖሚን በማጠናከር የአካባቢውን የቡና ምርት አቅም ለማሳደግ የሚጫወተው ሚና የጎላ ነው።

በዚህም መነሻነት የቡና ችግኝ ማፍላት፣ በተገቢው የአተካከል ዘዴ መትከል፣ የእርሻ እንክብካቤን ማጠናከር እና የተቀናጀ የቡና ልማትን ማስፋፋት ለቀጣይ የምርት ዕድገት ወሳኝ ናቸው።

በሙዳ–ድኖቆሰ ቀበሌ የሚታየው ይህ የቡና ልማት ገጽታ በጓሮ ልማት የተሻለ ምርትና የተሻለ ገቢ ለማምጣት የሚቻል መሆኑን የሚያሳይ አበረታች ምሳሌ ነው።

መረጃው የሙደ ድኖቆሳ ቀበሌ ግብርና ጽ/ቤት ነው።
August 30, 2026 713 2