ተቋሙ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ለአጀንዳ 2030 ግብ መሳካት ቁርጠኝነቱን እያሳየ ይገኛል" - ቶሎሳ… — Dilla University Official — TG.ME

"ተቋሙ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ለአጀንዳ 2030 ግብ መሳካት ቁርጠኝነቱን እያሳየ ይገኛል" - ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር)
===========*************============

ዲ.ዩ: ነሐሴ 11/12/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)

በዲላ ዩኒቨርሲቲ በመደራጀት ላይ የሚገኙ የስማርት መማሪያ ክፍሎች ያሉበትን ደረጃ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር) ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በዩኒቨርሲቲው በአራቱም ጊቢዎች እጅግ ዘመናዊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች የተሟላላቸው የስማርት መማሪያ ክፍሎችን በማደራጀት ለመጪው የትምህርት ዘመን ዝግጁ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

ፕሬዝዳንቱ በሀሴዴላ ጊቢ እና በማስተማሪያ ሆስፒታሉ ፕሮጀክቱ የደረሰበትን ደረጃ የተመለከቱ ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በማደራጀት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ለአጀንዳ 2030 ግብ መሳካት ቁርጠኝነቱን እያሳየ እንደሚገኝ አውስተዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም ፕሮጀክቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ እና ክትትል እንደሚደረግም ገልፀዋል።

ዲላ ዩኒቨርሲቲ በአዲሱ የትምህርት ዘመን፣ በርካታ አዳዲስ የትምህርት ግብዓቶችን በማሟላት ተማሪዎቹን ለመቀበል ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ስለመሆኑ ተገልጿል።

===###===

#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ
#UniversityOfTheGreenland
❤28👍1
August 17, 2026 5.8K 3