ፍርድ የእግዚአብሔር ነው፡፡ እኛ ግን ወንድሞቻችን ላይ በመጨከን ስንት ጊዜ በክርስቶስ የፍርዱ ዙፋን ላይ… — Dn Abel Kassahun Mekuria — TG.ME

ፍርድ የእግዚአብሔር ነው፡፡ እኛ ግን ወንድሞቻችን ላይ በመጨከን ስንት ጊዜ በክርስቶስ የፍርዱ ዙፋን ላይ ተቀመጥን? የሰውን ድካም ሳንረዳ ፈጥነን በመፍረድ ስንት ጊዜ ራሳችንን በእግዚአብሔር ቦታ አስገባን? እስኪ ዮሴፍን እናስበው፡፡

ወደ ግብጽ ባሪያ አድርገው በግፍ የሸጡት ወንድሞቹ ከአባታቸው ሞት በኋላ እርሱ ወደ ተሾመበት ግብጽ መምጣት በፈለጉ ጊዜ፣ የክፋታችንን ብድራት ያስከፍለናል ብለው ስለፈሩ ‹‹በደላችንን ተውልን›› ሲሉ መልእክተኛ ልከውበት ነበር፡፡ የዋሁ ዮሴፍም ይህንን ሲሰማ እያለቀሰ እንዲህ አላቸው ‹‹አትፍሩ፤ እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን?››፤ አይደለም ሳታውቀው ዐውቀኸው እንኳን በበደለህ ወገንህ ላይ ለመፍረድ ልብህ በከጀለህ ጊዜ ለራስህ የዮሴፍን ጥያቄ ጠይቀው፡፡

‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን?›› (ዘፍ 50፡19)

ዲያቆን አቤል ካሣሁን
[email protected]
❤193🙏34😢11✍6👍5🔥2🥰2👏1👌1
August 12, 2026 6.9K 1 36