በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በግብጽ ስለ ተፈጸመ አንድ ታሪክ ላስታውሳችሁ። በላዕላይ ግብጽ ይኖር የነበረ… — Dn Abel Kassahun Mekuria — TG.ME

በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በግብጽ ስለ ተፈጸመ አንድ ታሪክ ላስታውሳችሁ። በላዕላይ ግብጽ ይኖር የነበረ አንድ ምስጉን ካህን በጊዜው የከተማው ከንቲባ ወደ ሆነው ባለሥልጣን ቢሮ ሄዶ ቤተ ክርስቲያንን በሚመለከት ለከንቲባው ጥያቄ ያቀርብለታል። ይሁን እንጂ ከንቲባው ግን በንቀት ያን የእግዚአብሔር ካህን እያመናጨቀ በጥፊ መትቶ ከቢሮው ያስወጣዋል። በዚህ ድርጊት እጅግ ልቡ ያዘነውም ካህን እንባውን እያፈሰሰ ለአገልግሎት ወደሚጠበቅበት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ የጸሎት ሥርዓቱን አስጀመረ። ካህኑ በቤተ ክርስቲያን ሆኖ ሲጸልይ ሳለ ያ ከንቲባ በመንገድ ሲሄድ ድንገት ዙሪያው ጨለመበት፣ በፈረስ የተቀመጠ አንድ ሰውም ከመንገዱ አስቁሞ "ለምን ካህኑን እንደዚያ አዋርደህ ሰደብህ?" ሲል ጠየቀው። ከንቲባውም ገና መልስ መስጠት ሳይጀምር ያ ፈረሰኛ ፊቱን በጥፊ ጸፋው። ከምቱ ጥንካሬም የተነሣ አንድ ዓይኑ ጠፋ። ይህ እንደ ሆነም ወዲያው ጨለማው ተገፈፈ። ያ ፈረሰኛ ማን ነው?

ካህኑ ሄዶ እንባውን ካፈሰሰለት ከሰማዕቱ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ውጭ ማን ሊሆን ይችላል።



ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
አዲስ አበባ
❤238🥰14🙏8🔥5👍4👏4🤩1
August 25, 2026 4.3K 7 21