የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጲያ የንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ጋር በትብብር ለመስራት ተስማማ፦ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ነጻ የንግድ ማማከር አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል ያቋቁማል::
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጲያ የንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ጋር በትብብር መስራት የሚያስችለውን ውይይት ከንግድ ምክር ቤቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር አድርጓል፡፡ ሁለቱ ተቋማት በማማከር እና ስልጠና፣ በምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም የተለያዩ ኮንፍረንሶችን በትብብር ማዘጋጀት በሚችሉበት ጉዳይ ዙሪያ መክረዋል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተማም አወል በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፤ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ አምራች እና አገልግሎት ሰጪ ኢንዱስትሪዎች ጋር በመቀራረበ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይነትም በተለይ አዲስ የቢዝነስ ሀሳብ ያላቸውን ስራ ፈጣሪዎች እንዲሁም ስራ ነክ ጉዳዮች ላይ ነፃ የቢዝነስ ማማከር አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል እንደሚከፍት ይፋ አድርገዋል፡፡
የኢትዮጲያ የንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ዋና ፀኃፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ በበኩላቸው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ምርምሮችን የመስራት ልምድ እና እውቀት ያላቸው ምሁራን መገኛ መሆኑን ገልፀው ምክርቤቱ ይህንን አቅም ለመጠቀም ከትምህርት ተቋማቱ ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ዘርፍን የትኩረት አቅጣጫ በማድረግ እና የሰለጠነ የሰው ሃይል አብቅቶ ለስራ ከማቅረቡም በላይ የንግዱን ማህበረሰብ፣ አምራች እና አገልግሎት ሰጪ ኢንዱስትሪዎችን እንዲሁም አዳዲስ የቢዝነስ ሃሳብ ያላቸውን ስራ ፈጣሪ ወጣቶችን እና ተማሪዎችን የሚደግፉ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ በመድረከ ተመላክቷል፡፡
12
2
1
1
1August 21, 2026 5K 2

