በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል እየተከናወኑ ያሉ የክረምት በጎ አድራጎት ሥራዎች በድሬዳዋ… — Dire-Dawa University — TG.ME

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል እየተከናወኑ ያሉ የክረምት በጎ አድራጎት ሥራዎች

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል የ2018 ዓ.ም. የክረምት በጎ አድራጎት መርሃ ግብሮች በተለያዩ የድሬዳዋ አስተዳደር አካባቢዎች በሰፊው እየተከናወኑ ይገኛሉ። በዛሬው እለት የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንቶች፣ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና የሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር፣ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር በአሸዋ አላይ-በዴ አካባቢ የተካሄደውን የበጎ አድራጎትና የሕክምና አገልግሎት መርሃ ግብር ጎብኝተዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ወቅትም ለማህበረሰቡ ነጻ የህክምና ምርመራ፣ የጤና ምክር አገልግሎት እንዲሁም የማህበረሰቡን ግንዛቤ ለመጨመር የጤና ትምህርት ተሰጥቷል። በጉብኝቱ ላይም መልዕክት ያስተላለፉት የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅና የሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኪዮቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ሁሴን መሀመድ መርሀ ግብሮቹ በቀጣይ በአስተዳደሩ የገጠር አካባቢዎች እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
❤27🥰4👏3
August 12, 2026 6.6K 3