አወድሶ ነጣይነት እና አኮስሶ ገፊነት ይቁም !!
የአማራ ፋኖ በየአካባቢው ከጠላት ጋር የሚያደርገው ጦርነት የሕልውና እንዲሁም የፍትሕ ርትዕ መሆኑ የታወቀ ነው።
ለዚህ ደግሞ የጦርነቱን እድሜ የሚያሳጥሩ ዘመቻዎችን ያካሒዳል።
ለምሳሌ በጎጃም የታወጀው ዘመቻ አላማ ጦርነቱን በማሳጠር ህዝቡ የሚከፍለውን መስዋዕትነት ማሳጠር እና የወገንን ወታደራዊ ብልጫ ማረጋገጥ ነው !!
ይሔ በየትኛውም አካባቢ በተለያየ ቅርፅ ተግባራዊ እየሆነ ያለና የሚገባ ነው !!
ይሔንን ዘመቻ ለመደገፍ ግን ነጥሎ ማወደስና ነጥሎ የማሳነስ ቃና ያለው መረጃና አስተያየት ማቅረብ ማንንም አይጠቅምም።
ለጀመሩት ልዩ ዘመቻ እና ዘመቻውን እየመሩ ላሉበት ጥበብ የአማራ ፋኖ በጎጃም አመራሮችን ክብር መስጠት ይገባል::
ታዲያ በሌላው ቀጠና ያለው የፋኖ አመራርም በተመሳሳይ ግለት ትግሉን እንዲገፋበት በሚያደርግ መንገድ አጀንዳውን ለህዝብ ማድረስ ይገባል እንጅ አንዱን ከፍ አድርጎ ሌላውን ማጣጣል አያስፈልግም::
የትኛውም ቀጠና ላይ በአማራ ጠላቶች ላይ የሚያርፍ ዱላ የሁሉንም አማራ አንገት ቀና ያደርጋል እና ፕሮፖጋንዳው ይህንን ሐቅ ለአፍታም እንዳይዘነጋ !!
ድጋፍህ በአማራ ብሔርተኝነት ርዕዮት ተጋድሎ እያደረገ ካለው የአማራ ሕዝብ ጋር መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም።
አካባቢ ለይቶ በማወደስ ስም ተነጣይነትን ማስተጋባት ኢ-ፖለቲካዊ ነው።
አወድሶ ነጣይነት አኮስሶ ገፊነት አይጠቅመንም !!
ማስተዋል ይገባል።
ጎጠኛ አቆርቋዥነትንም ፣ በዜግነት የተጀቦነ ትግል ቀልባሽነትንም በአማራነት ርዕዮትና መስመር እናሸንፋለን ‼
#ድል ለአማራ ትግል !!
#AmharaRevolution
4
2
1August 15, 2024 2.8K 1