📌ድህነትን ሳይሆን ድሃን የሚጠየፈው ፋሽታዊው የብልጽግና አገዛዝ በሚከተለው የጦርነት ፖሊሲ ኢትዮጵያ የምድር ሲዖል ሆናለች።
በተለየ ሁኔታ አዲስ አበባ ደሃ የማይኖርባት ከተማ ሆናለች። ከደሃ አልፎ መካከለኛ ገቢ የነበራቸው የኀብረተሰብ ክፍሎች መኖር የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
• በድህነት ወለል የሚኖረው ዜጋ በከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ይገኛል፡፡ በከተሞች በገባው ረሃብ ራሳቸውን የሚያጠፉ ዜጎች ቁጥር በመጨመር ላይ ነው፡፡ የሴተኛ አዳሪዎች ቁጥር በእጥፍ እንደጨመረ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ያሰያሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ባለፉት ሦስት ዓመታት 60 ሺህ አዳዲስ ሴተኛ አዳሪዎች ገበያውን እንደተቀላቀሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሶሺዎሎጅ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች ጥናት ያሳያል፡፡
የመንግሥት ሰራተኛ የሆኑ ሴቶች በትርፍ ሰዓታቸው በዚህ ሕይወት ተሰማርተው ኑሯቸውን ለመደጎም እንደተገደዱ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
በኑሮ ውድነት ጫና በርካታ ዜጎች ስቃይ ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ አዲስ አበባን በመሰሉ ትልልቅ ከተሞች ራሳቸውን የሚያጠፉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡
አዲስ አበባ በቂ አብዩታዊ ሁኔታ ላይ ነች👇
• የኑሮ ውድነቱ 400% ጭማሪ የታየባት፤
• በኦሕዴድ ዘረኛ አገዛዝ ተቀፍድዳ የተያዘች፤
• ከሕዝብ ኪስ የተሰረቀች ከተማ፣
• ቤተሰቡን ማስተዳደር ያልቻለ የዩኒቨርሲቲ
መምህር የሚኖርባት፤
• እንደመጤና ሰፋሪ የሚታይ በግብር ጫና
ወገቡ የጎበጠ ነጋዴ፤
• ማንነት ወንጀል ሆኖ እየተሳደደ የሚታሰር
በሚሊዩን የሚቆጠር አማራ የሚኖርባት፤
• በፋሽስቱ የጦርነት ፖሊሲ የተፈጠረው ጦርነት በፈጠራቸውና እየፈጠራቸው ባሉ ጫናቸው የተነሳ፣ በምርት መራቆት፣ በገበያ ትስስር እጦት፣ በኃይል እጥረት በርካታ ኢንዱስትሪዎቿ የተዘጉባት፤ በሺህ የሚቆጠሩ ሰራተኞች ተቀንሰው የጎዳና ኑሮ ላይ የወደቁባት፤
• ዜጎች ከመኖሪያ ቤታቸው እየተነቀሉ ችግኝ
የሚተከልባት፤
• 30ሺሕ የኦሕዴድ ቢሊየነሮችን ለማፍራት ግብ ተቀምጦ፤ የአማራ፣ የጉራጌ፣ የትግሬ፣ ባለሃብቶች የሚሳደዱባት፤
• የዐቢይ አሕመድ የግል ጀኔራሎች ለማህበራዊ ብልግናቸው ለአንዲት ሴት እስከ 3 ሚሊየን ብር ከፍለው በሚዝናኑበት ከተማ፤
➽ መቶ ሺህዎች በከተማ ረሃብ የሚሰቃዩበት፤
➽ ጨርቅ አስጥሎ የሚያሳብዱ ማኀበራዊ ቀውሶች የበዙባት አዲስ አበባ ለሕዝባዊ አመፅ በቂ ምክንያት አላት…!!
★ በአዲስ አበባ ከተማ በማንኛውም ቀንና ሰዓት
ሕዝባዊ አመፅ ይነሳል…!!
★ ለከተማ ግንባር ዕድል ሆኖ መግቢያ በሩን
እያንኳኳ ያለው ሕዝባዊ ማዕበል ግባ በለው
ሊባል ይገባል…!!
#ቤተመንግሥቱንመያዝ #Occupythepalace #ፋኖ #EndFascism #በቃ #peoplepower
ኢትዮ 251 ሚዲያ
የነጻነት አንደበት!
Forwarded fromMulugeta Anberber

7August 6, 2024 2.4K 1