ሪያል ማድሪድ በሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፍ ችሏል:: በስፔን ላሊጋ ተስተካካይ መርሐ ግብር ሪያል ማድሪድ… — @Banchi Abera ከሰበታ💚💛❤ — TG.ME

ሪያል ማድሪድ በሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፍ ችሏል::

በስፔን ላሊጋ ተስተካካይ መርሐ ግብር ሪያል ማድሪድ ሳንቲያጎ ቤርናባኦ ላይ ሪያል ሶሴዳድን ገጥሞ 4ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ የቻለ ሲሆን በጨዋታው ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ሀትሪክ መስራት ችሏል። የሎስ ብላንኮስን ቀሪ ጎል ቪንሰስ ጁኒየር ከመረብ ሲያሳርፍ ለሪያል ሶሴዳድ ሱቺች ብቸኛዋን ግብ አስቆጥሯል።

በጨዋታው ጁድ ቤሊንግሀም በጨዋታው ሁለት ለግብ የሆነ ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ሲችል ውጤቱን ተከትሎ የሆዜ ሞሪንሆ ቡድን 6 ነጥቦችን ሰብስቦ ሊጉን መምራት ጀምሯል::
August 26, 2026 84