የእግዚአብሔር ልጆች ነን? ወይስ የእግዚአብሔር ጉዲፈቻ ልጆች ?
የማንነት ቀውስ ውስጥ እንዳንገባ ፣ ቃሉን ጠንቅቀን እናጥና።
አንዳንድ ጊዜ አንድን እውነት ለማፅናት ስንል፣ ሌላ እውነት እናፈርሳለን።
መፅሐፍ ቅዱስ የሚያቀርብልንን እውነት ሁሉ እንዳለ እንቀበለው። አንዱን ሀሳብ ከሌላው ሀሳብ ጋር ከማጋጨት ይልቅ እንደተፃፈው በአውዱ አጥንተን ለመረዳት መሞከር ይሻላል እንጂ አላስፈላጊ ክርክር ውስጥ ለምን እንገባለን?
ሰሞኑን አንዳንድ ቪዲዮዎችን ስመለከት ነበር። ጉዲፈቻ ነን ወይስ አይደለንም እየተባለ በዚህ ጥያቄ ዙሪያ ላይ የቀረቡ አንዳንድ ሀሳቦችን ስሰማ ነበር።
ጥቂት ሀሳቦችን ላንሳ!
ስለ እኛ የእግዚአብሔር ልጅነት ከመናገራችን በፊት ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልጅነት ጥቂት እንመልከት።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር አንድያ ልጁ መሆኑን ልብ እንበል።
አንድያ ልጁ ነው ስንል ምን ማለታችን ነው? He is the ONLY begotten Son of the Father! ማለታችን ነው። የእግዚአብሔር ብቸኛ የባህሪ ልጁ ነው ማለታችን ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን “The Son of God” የሚለው title መለኮትነቱን (deity) መሆኑን የሚያሳይ ነው።
“For God so loved the world, that He gave His only begotten Son, that whoever believes in Him shall not perish, but have eternal life.
— John 3:16”
16“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወድዷልና።”
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ከመባልም ባሻገር በተለያዮ ስያሜዎች ተጠርቷል።
ጥቂቶቹን ለመግለፅ
“…ስሙንም ኢየሱስ ብለህ ትጠራዋለህ፤ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና።” ማቴ 1:21
ኢየሱስ ማለት አዳኝ (Savior) ማለት ስለሆነ፣ አዳኝ ተብሏል፣ ክርስቶስ (የተቀባው) መሲሁ የሚል Title ተሰጥቶታል። የእግዚአብሔር አገልጋይ ተብሎ ተጠርቷል (ኢሳያስ 42:1) ፣ነቢይ፣ ካህን ፣ ንጉስ፣አማላጅ፣ የአብርሐም ልጅ፣ የዳዊት ልጅ (ማቴ 1:1 )ተብሎም ተጠርቷል። ከዚህ በላይ ብሎ ስሞችና ስያሜዎች ተሰጥቶታል። እነዚህ ሁሉ እውነት ናቸው።
🚩ልብ በሉ! ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ስለሆነ የዳዊት ልጅ አይደለም አይባልም። መፅሐፍ ቅዱስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የአብርሐም ልጅ ወይም የዳዊት ልጅ ብሎ ለምን ጠራው ብለን ቃሉንና ሀሳቡን ለመረዳት እንሞክራለን እንጂ ፣ አንድን እውነት ለማፅናት ብለን ሌላ እውነት አናፈርስም።
“1የዳዊት ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ የሚከተለው ነው።”ማቴ 1:1
🚩አዋ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ተብሎ ተጠርቷል! መፅሐፍ ቅዱስ ይሃንን ስያሜ ሲሰጠው አልተሳሳተም። ለምን የዳዊት ልጅ ተባለ የሚለውን ሀሳብ ለመረዳት መፅሐፍ ቅዱስን አጥኑ እንጂ ቃሉ በግልፅ ያስቀመጠውን እውነት አናፍርሰው።
“3ወንጌሉም ስለ ልጁ፣ በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለሆነ፣ 4በቅድስና መንፈስ ደግሞ ከሙታን በመነሣቱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ በኀይል ስለ ተገለጠው ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።” ሮሜ 1:3
እዚ ጋር ጳውሎስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሲገልጠው በስጋ “ከዳዊት ዘር ስለሆነ” ይለውና “ በቅድስና መንፈስ ደግሞ ከሙታን በመነሳቱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ በሀይል ስለተገለጠው ስለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ” ነው ወንጌል ይለናል።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዳዊት ልጅ የተባለበትን ምክንያት እዚህ ጋር ያሳየናል።
አይነ ስውር የነበረው በርጠለሚዎስ የዳዊት ልጅ ሆይ ማረኝ እያለ ደጋግሞ ሲጮህ እንደነበረ መፅሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንደፈወሰው፣ አይኑን እንዳበራለት እናስታውሳለን።
ለምን የዳዊት ልጅ ብሎ ጠራው? ከዳዊት የዘር ሀረግ የሚመጣ መሲሁ ይጠባበቁ ስለነበር፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሲሁና ንጉስ መሆኑን በልቡ ስለተረዳ ነው “የዳዊት ልጅ ሆይ ማረኝ” እያለ ሲጮህ የነበረው። ይሄንንም እውነት የገለጠለት እግዚአብሔር ነው።
አንድ በደንብ ልናስተውለው የሚገባ እውነት ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ እኛ (adopted) ወይም ጉዲፈቻ ልጅ አለመሆኑን ነው። እኛ ስል በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነን በመንፈስ ቅዱስ ዳግም ተወልደን የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆን ስልጣን የተሰጠንን ሰዎች ማለቴ ነው።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መለኮት ነው። የእግዚአብሔር ብቸኛና አንድያ የባህሪ ልጁ ነው። አማኑኤል (እግዚአብሔር ከኛ ጋር) የምንለው እግዚአብሔር ወልድ፣ ዘላለማዊ አምላክ፣ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ልጅ፣ አልፋና ኦሜጋ፣ የመጀመሪያና የመጨረሻ፣ የክብር ጌታና የነገስታት ንጉስ ነው።
——————————————————————
ወደ እኛ ደግሞ ስንመጣ የእግዚአብሔር ልጅ ነን ወይስ ጉዲፈቻ የሚል ክርክር ውስጥ ለምን ገባን?
ለምን ሀሳቡን (either or) አደረግነው? ነጭ ያልሆነ ሁሉ ጥቁር ነው። ጥቁር ያልሆነ ሁሉ ነጭ ነው ብሎ እንደመከራከር ያህል ነው። ሌሎች ከለሮችን ከግምት ውስጥ ሳናስገባ።
በመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርት አውዱን ጠብቀን ስናጠና ጉዲፈቻ መባላችን ወይም (adopted) የሚለው ሀሳብ የእግዚአብሔር ልጆች ከመሆናችን ጋር የሚጋጭ ወይም የሚቃረን ሳይሆን እንዲያውም የልጅነት ስልጣናችንን የሚያረጋግጥና የሚያፀና ትልቅ እውነት ነው። በርግጥ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን መጠራታችን የእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅርን የሚገልፅልን እውነት ነው።
“1የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ አብ አትረፍርፎ ያፈሰሰልን ፍቅር ምንኛ ታላቅ ነው! እኛም እንዲሁ ልጆቹ ነን” 1 ዮሀንስ 3:1
Westminister Confession of Faith (chapter 12)
“ All those that are justified, God vouchsafeth, in and for His only Son Jesus Christ, to make partakers of the grace of adoption, by which they are taken into the number, and enjoy the liberties and privileges of the children of God, have His name put upon them, receive the Spirit of adoption, have access to the throne of grace with boldness, are enabled to cry, Abba, Father, are pitied, protected, provided for, and chastened by Him as by a Father; yet never cast off, but sealed to the day of redemption, and inherit the promises, as heirs of everlasting salvation.”