ቲቪ ስንጠቀም የሚጠቅሙ ጥንቃቄዎች፦
1. ቲቪውን በትክክለኛ ቮልቴጅ ይጠቀሙ
የኤሌክትሪክ መውጫ መቆጣጠሪያ (Stabilizer/Surge Protector) መጠቀም ይመከራል።
2.ከውሃና ከእርጥበት ያርቁ
ውሃ ወይም እርጥበት ቦርድን ሊያበላሽ ይችላል።
3.የአየር መግቢያውን አትዝጉ
ቲቪው እንዳይሞቅ ከጀርባው አየር እንዲያልፍ ቦታ ይተዉ።
4.ለረዥም ጊዜ ሰዓታት አይጠቀሙ
ኤሌክትሪክ ለመቆጠብና የቦርድ እድሜ ለማራዘም ይረዳል።
5.ስክሪኑን በጠንካራ ነገር አትንኩ
LCD/LED ስክሪን በቀላሉ ሊሰበር ይችላል።
6.በትክክል ያጽዱ
ለስላሳ ጨርቅ ብቻ ይጠቀሙ፤ ቀጥታ ውሃ ወይም ኬሚካል አትርጩ።
7. ልጆች እንዳይጥሉት በደንብ መቀመጡን ያረጋግጡ
ግድግዳ ላይ በደንብ ይስቀሉ ወይም በጠንካራ ጠረጴዛ ላይ ያስቀምጡ።
8.በመብረቅ ጊዜ ሶኬት ይንቀሉ
የኤሌክትሪክ ጉዳት እንዳይደርስ ይከላከላል።
9.ያልተለመደ ሽታ ወይም ድምፅ ካለ
ወዲያውኑ ያጥፉና ባለሙያ ያሳዩ።
10.ብራይትነስና ድምጽ ከመጠን በላይ አያድርጉ
የስክሪን እድሜንና የጆሮ ጤናን ይጠብቃል።
JOIN👇👇👇
@computer_mobile21
@seen311
9
1May 21, 2026 3.4K 1 6