የግንባታውን ዘርፍ አዲስ ገፅታ እያላበሰ የሚገኘው የሞዱላር (3D) ቴክኖሎጂ
****
በቻይና የመኖሪያ ቤቶች እና የኢንዱስትሪ ሕንጻዎች የሚገነቡበት መንገድ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አዲስ መልክ እየያዘ ይገኛል።
ሀገሪቱ የሞዱላር (3D) ቴክኖሎጂን በመጠቀም የቤቶችን ክፍሎች በፋብሪካ አምርቶ የመገጣጠም ዘዴን በስፋት እየተገበረች ሲሆን፣ ይህም የግንባታውን አቅምና ፍጥነት በእጅጉ ጨምሮታል።
ይህ ስልት ግንባታን ከተለመደው አድካሚ አሠራር ወደ ዘመናዊ የፋብሪካ ምርትነት በመቀየር ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ሲሆን፣ ለኢንዱስትሪውም አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል።
በዚህ ዘመናዊ አሠራር ደንበኞች የሚፈልጓቸውን የቤት ዓይነቶች፣ ዋጋ እና ዲዛይን ባሉበት ሆነው በኢንተርኔት መምረጥ ይችላሉ።
ደንበኛው ምርጫውን ካሳወቀ በኋላ ቤቶቹን የሚሠራው ድርጅት በፍጥነት ወደ ሥራ የሚገባ ሲሆን፣ ከግንባታው ሥራ 90 በመቶ የሚሆነው ክፍል በፋብሪካ ውስጥ በከፍተኛ ጥንቃቄ ተመርቶ ደንበኛው በፈለገው ቦታ ላይ እንዲገጣጠም ይደረጋል።
ይህ አሠራር የግንባታ ጊዜን በ75 በመቶ፣ የካርቦን ልቀትን በ30 በመቶ፣ እንዲሁም የአቧራና የድምፅ ብክለትን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል።
JOIN👇👇👇
@computer_mobile21
@seen311

6
2April 23, 2026 3.1K 2 1