ChatGPT "ጅል" እንዳይሆንባችሁ
ChatGPT እውነተኛ ረዳት እንዲሆንላችሁ ከፈለጋችሁ፣ እናንተን እንዲሞግትና ስህተታችሁን እንዲያርም በ "Custom Instructions" ማዘዝ ትችላላችሁ ።
🎯 ChatGPT ላይ Settings ውስጥ ይግቡ ።
🎯 Personalization የሚለውን መርጠው Custom Instructions የሚለውን ይክፈቱ።
🎯 "How would you like ChatGPT to respond?" በሚለው ሳጥን ውስጥ የሚከተለውን ትዕዛዝ ኮፒ አድርገው ያስገቡ፦
"ሁልጊዜ እኔን ለማስደሰት ብቻ አትሞክር። ስህተት ከሰራሁ በግልጽ ንገረኝ፣ ሃሳቤን ሞግተው (Challenge me)፣ እና ከተለመደው ውጭ ያሉ አዳዲስ አማራጮችን አቅርብልኝ። እንደ ጅል 'አዎ' ባይ ሳትሆን እንደ ጥብቅ መምህርና አማካሪ ሁን ።"
[ ይህን instruction comment ላይ በ English ጭምር አሰቀምጣለሁ check comment section ]
🎯 የዚህ ሴቲንግ 3 ጥቅሞች፦
1. ከስህተት ያድናችኋል፦
የሆነ ጽሁፍ ጽፋችሁ "እንዴት ነው?" ስትሉት "ቆንጆ ነው" ከማለት ይልቅ "እዚህ ጋር ተሳስተሃል፣ ይሄኛው ሃሳብህ ደካማ ነው" ብሎ እውነቱን ይነግራችኋል።
2. አዳዲስ ሃሳቦችን ያፈልቃል፦
የእናንተን ሃሳብ ብቻ ከመድገም ይልቅ "ይህንን ነገር በዚህ በኩል ለምን አታየውም?" በማለት የተሻለ መንገድ ያሳያችኋል።
3. የሃሳብ ጥራት ይጨምራል፦
የሚሞግታችሁ ሰው ሲኖር ሃሳባችሁን ይበልጥ እንድታጠሩና ጠንካራ ስራ እንድትሰሩ ያደርጋችኋል።
"አንድ ትልቅ ሚስጥር፦
ChatGPT እንደ መስታወት ነው። የጠየቃችሁትን ያህል ነው የሚመልሰው። 'ብልጥ' ጥያቄ ከጠየቃችሁት 'ብልጥ' መልስ ይሰጣችኋል፤ ዝም ብላችሁ 'እሺ' ካላችሁት ግን ጅል ሆኖ ያርፋል!

18
16
1
1March 4, 2026 4.6K 8 24