አንድ የተጠየኩት ጥያቄ አለ እሱም
አንድ ዘማሪ የማናውቀውን መዝሙር ቢዘምር ኮርዱን ስለማናውቀው እንዴት አርገን ነው ምናጅበው የሚል ጥያቄ ነው
መልሱ
Chord progression ዝም ብላችሁ አጥኑ የምለው ለዚህ ነው የሚታወቅም የማይታወቅም መዝሙር አንድ የሚያመሳስላቸው ነገር አለ እሱም አብዝኛው የ መዝሙሮቻችን movement ተመሳሳይ ነው ወይ ተቀራራቢ ነው ስለዚህ ከዚህ በፊት የምታውቁትን chord progression ለዚኛው መድረክ ላይ እየተዘመረ ላለው አዲስ መዝሙር ነው ላላችሁት መጠቀም ትችላላችሁ መጀመሪያ just የመዝሙሩን movement አዳምጡ ስትሰሙት ከሆነ መዝሙር chord movement ጋር ይቀራረባል so አንድ ይሄን technique ተጠቀሙ
Possible የሆነ ተቀራራቢ chord ይሆንላቹሃል
ሁለተኛው technique ደግሞ የማታውቁት መዝሙር ሲዘመር ያው ግድ በደንብ ጥሩ ጆሮ ያስፈልጋቹሃል ዘማሪው ድምፁ ወዴት እየሄደ እያረፈ እንዳለ በደንብ ማወቅ አለባችሁ ወደዚህ ደረጃ ምትመጡት ደግሞ
Ear👂training ስትሰሩ ነው like
Interval practice አድርጉ
ከ C ወደ E ያለው feeling እና ድምፅ ከ E ወደ G ያለው የድምፅ taste or interval በደንብ practice አድርጉ ጆሮአችሁ ውስጥ እስኪቀር እና እስኪለምድ ድረስ 🤏
በ ትንሽ practice ብቻ ጎበዝ አትሆኑም ይሄን እወቁ ጥሩ ሙዚቀኛ መሆን ከፈለጋችሁ ዋጋ ክፍሉ በቃ ግድ ነው 😉
ማታውቁት መዝሙር ሲዘመር አትደንግጡ just በ ግምትም በምንም እየተጫወታችሁ ስህተታቹን ለማወቅ ሞክሩ እና እሱ ላይ ስሩ ሌላው
ሙዚቃ የልምድ እና የጊዜ ጉዳይ ነው አትቸኩሉ ሁሉም ነገር ቀስ በቀስ እየቀለለ እና እየገባችሁ ይሄዳል
That's it ✌️
ሌላ ጥያቄ ካላችሁ አሁንም ጠይቁ
@chordprogression
26
14July 6, 2026 2.2K 4 5